የአጠቃቀም መመሪያ

(መጨረሻ የተሻሻለበት 5 ግንቦት 2023 ዓ/ም)

1. ድረገጽ

1.1 የአገልግሎት መመሪያዉን መቀበል

ይህን ድረገጽ የመጠቀም ሂደት የእርስዎ እነዚህን የአጠቃቀም መመሪያ እና የእኛን ግላዊነት መግለጫ መቀበል ላይ የተመሰረተ ነዉ፡፡ ይህንን ድረገጽ መጠቀምዎን መቀጠልዎ እርስዎ የእኛን የአጠቃቀም መመሪያ እና ግላዊነት መግለጫ እንደተቀበሉ ተደርጎ ይወሰዳል፣ ይህም እርስዎ አባል ሆነዉ መመዝገብዎት ወይም አለመመዝገብዎት ላይ አይመሰረትም፡፡ እኛ እነዚህን የአጠቃቀም መመሪያ እና የእኛን ግላዊነት መግለጫ በየትኛዉም ጊዜ ላይ ልንቀይር እንችላለን፡፡ የምንቀይር ከሆነ፣ የተቀየረዉ የዘመን የአጠቃቀም መመሪያ እና ግላዊነት መግለጫ በድረገጹ ላይ የሚለጠፍ ይሆናል፡፡ እርስዎ የአጠቃቀም መመሪያ እና የግላዊነት መግለጫዉን በየጊዜዉ መመልከትዎን የማረጋገጥ ሀላፊነት አለብዎት፡፡ የድረገጹ አባል ከሆኑ እና የአጠቃቀም መመሪያዉ እና ግላዊነት መግለጫ ላይ የተደረጉት ለዉጦች ትኩረት የሚሹ ከሆነ፣ ባቀረቡት የመገኛ መረጃ አማካኝነት ስለ ለዉጦቹ እርስዎን ለማሳወቅ የተቻለንን ጥረት እናደርጋለን፡፡

እርስዎ በዚህ የአጠቃቀም መመሪያ ላይ የማይስማሙ ከሆነ ይህንን ድረገጽ መጠቀም የለብዎትም፡፡

1.2 በመገኛ አድራሻ ላይ የሚሞረኮዝ የአጠቃቀም መመሪያ

(ሀ) እርስዎ በአዉሮፓ ሕብረት በሚገኝ ሀገር ዉስጥ የሚኖሩ ከሆነ አንቀጽ 16.7 እና አንቀጽ 18.8(ሀ) እርስዎ ላይ ተፈጻሚ ይሆናሉ (ሆኖም ግን አንቀጽ 18.8(ለ) እርስዎ ላይ አይሰራም)፡፡
(ለ) እርስዎ የሚኖሩት በአዉሮፓ ሕብረት ዉስጥ የሚገኝ ሀገር ዉስጥ ካልሆነ ቀጽ 18.8(ለ) እርስዎ ላይ ተፈጻሚ ይሆናል (ነገር ግን አንቀጽ 18.8(ሀ) እርስዎላይ አይሰራም)፡፡
(ሐ) እርስዎ ቀጥሎ በተጠቀሱት ማንኛዉም የዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ ግዛት ዉስጥ የሚኖሩ ከሆነ፣ አንቀጽ 16.3(ሀ) እርስዎ ላይ ተፈጻሚ ይሆናል: አሪዞና፣ ካሊፎርኒያ፣ ኬነቲከት፣ ኤሊኖይስ፣ አዮዋ፣ ሚኒሶታ፣ ኒዉ ዮርክ፣ ኖርዝ ካሮላይና፣ ኦሀዮ ወይም ዊስኮንሰን፡፡
(መ) እርስዎ ቀጥሎ በተጠቀሱት ማንኛዉም የዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ ግዛት ዉስጥ የሚኖሩ ከሆነ፣ አንቀጽ 16.3(ለ) እርስዎ ላይ ተፈጻሚ ይሆናል: ካሊፎርኒያ፣ ኤሊኖይስ፣ ኒዉ ዮርክ፣ ወይም ኦሀዮ፡፡

1.3 የተጠቃሚ ዉል

እነዚህ የአጠቃቀም መሪያዎች የእርስዎን የአገልግሎቱን እና ድረገጽ አጠቃቀምዎን በሚመለከት በእርስዎ እና በድርጅቱ (ቀጥሎ በተገለጸው መሰረት) መካከል የተደረገን ዉል ያሰፍራል፡፡

1.4 ግንኙነት

ይህ ድረገጽ እንቅስቃሴዎቹ የሚከናወኑት Cupid Media Pty Ltd ሲሆን፣ ይህም በአዉስትራሊያ የተመዘገበ ድርጅት ነዉ፡፡ ድርጅቱ አዉሮፓ ሕብረት-ያልሆኑ ቢዝነሶች ኢ-አገልግሎቶች (VoeS) የተለየ መርሀ ግብር ስር ለአዉሮፓ ሕብረት ተጭማሪ እሴት ታክስ የተመዘገበ ነዉ፡፡ እኛን ከዚህ ቀጥሎ ባሉት በየትኛዉም ዘዴዎች ማግኘት ይችላሉ:

የኦንላይን ድጋፍ ቅጽ: እዚህ ጋር ይጫኑ (ለፈጣን አገልግሎት ይህን አማራጭ ይጠቀሙ)

ኢሜይል: teamAfroIntroductions.com

ስልክ ቁጥር: +61 7 5571 1181

ፋክስ ቁጥር: +61 7 3103 4000

በፓስታ: AfroIntroductions.com, PO Box 9304፣ Gold Coast MC, QLD 9726, Australia

ግላዊነትን በሚመለከት ጉዳይ ወይም የእርስዎ የግል መረጃ መሰብሰብ እና ጥቅም ላይ መዋልን በሚመለከት እኛን ለማግኘት፣ እባክዎትን የእኛን ግላዊነት መግለጫ ይመልከቱ፡፡

በአዉሮፓ ሕብረት በሚገኝ ሀገር ዉስጥ የሚኖሩ ከሆነ፣ VeraSafe የተባለ ድርጅት በአዉሮፓ ሕብረት ዉስጥ የመረጃ ጥበቃ ጉዳዬችን እንዲቆጣጠር በድርጅቱ ተወክሏል፡፡ ከላይ በተዘረዘሩት የእኛ መገኛ መረጃዎች አማካኝነት እኛን ከማግኘት ባለፈ፣ የእርስዎን ግላዊ መረጃዎች ማቀናበርን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ VeraSafe ድርጅትን ማግኘት ይችላሉ፡፡ እንደዚ አይነት ግንኙነት ለመፍጠር፣ እባክዎትን VeraSafe ድርጅትን በዚህ የማግኛ ቅጽ ያግኙ: https://www.verasafe.com/privacy-services/contact-article-27-representative.

በተዘዋዋሪም፣ VeraSafe ድርጅትን ከዚህ ቀጥሎ ባሉት አድራሻዎች ማግኘት ይቻላል:

ስም: VeraSafe Czech Republic s.r.o
አድራሻ: Klimentsk6 46 Prague 1, 11002 Czech Republic፤ ወይም

ስም: VeraSafe Ireland Ltd
አድራሻ: Unit 3D North Point House, North Point Business Park, New Mallow Road, Cork T23AT2P, Ireland፡፡

2. አባልነት

2.1 ብቁነት

በዚህ ድረገጽ ላይ አባል ሆነዉ ለመመዝገብ ወይም ድረገጹን ለመጠቀም ከ 18 ዓመት እድሜ በላይ ሊሆኑ ይገባል፡፡ ድረገጹን በመጠቀም፣ እርስዎ ይህን ዉል የመዋዋል መብት፣ ስልጣን እና ብቃቱ እንዳለዎት እና ሁሉንም የአጠቃቀም መመሪያዎች እንደሚከተሉ፣ መወከልዎ፣ ግዴታ እንዳለብዎት እና ዋስትና መስጠትዎን ተቀብለዋል፡፡

2.2 የዉል አፈጣጠር

አባል ሆነዉ በመመዝገብ ከክፍያ ነጻ ወይም ነጻ ላይሆን ከሚችለዉ ድረገጹን በተመለከተ ከድርጅቱ ጋር ዉል ገብተዋል፡፡ የአባልነት ጥቅሞችን ልዩ ገጽታዎችን ከፍ ወዳለ ደረጃ መዉሰድ ይችላሉ፡፡ የተወሰኑ ጥቅሞችን እና ልዩ ገጽታዎችን እና የዉል አንቀጾችን እንዲመርጡ እና የክፍያ መንገድ እንዲመርጡ ይፈለጋል፡፡ አባልነትዎን ከፍ ወዳለ ደረጃ በሚወስዱበት የመጨረሻዉ ምዕራፍ ላይ "ክፍያ ፈጽም" የሚለዉን ቁልፍ በመጫን፣ በተጠቀሰዉ ክፍያ ዋጋ ላይ የተመረጠዉ ከፍ ያለ የአባልነት አማራጭን በተመለከተ እርስዎን እና ድርጅቱን የሚያስማማ ዉል የሚገቡ ይሆናል፡፡

2.3 አባልነት

(ሀ) ያለ ምንም ክፍያ የአገልግሎቱ አባል መሆን ይችላሉ፡፡ ከክፍያ ነጻ የሆነዉ አባልነት በአገልግሎቱ የሚገኙ የተወሰኑ ልዩ ገጽታዎችን እና ጥቅሞች ላይ ብቻ መሳተፍ እንዲችሉ ያስችልዎታል፡፡ ተጨማሪ ጥቅሞችን እና ልዩ ገጽታዎችን ለማግኘት፣ ለአገልግሎቱ ክፍያ የሚፈጽም አባል መሆን አለብዎት፡፡ ስለሆነም፣ ተጨማሪ ጥቅሞች እና ልዩ ገጽታዎችን የመጠቀምዎ ሁኔታ ተገቢዉ ለሆኑት ክፍያዎች በሚፈጽሙጸት ክፍያ ላይ ይወሰናል፡፡
(ለ) ለዚህ ድረገጽ ተጠቃሚዎች ከለላ ለመስጠት፣ እርስዎ ፍርድ ቤት ሊያስቀርብ የሚችል ጥፋት ወይም ወንጀል ፈጽመዉ ከሆነ ድረገጹ ላይ አባል ለመሆን አያመለክቱም ወይም አባል እንደማይሆኑ እዉቅና ሰጥተዋል፡፡ ለአባልነት ማመልከቻ በማስገባት እርስዎ ከዚህ ቀደም ፍርድ ቤት ሊያስቀርብ የሚችል ጥፋት ወይም ወንጀል አለመፈጸምዎን እና በየትኛዉም የመንግስት ባለስልጣን በኩል የወሲባዊ ተንኳሽ ተብለዉ እንዲመዘገቡ አለመደረግዎን ለእኛ ዋስትና እና ዉክልና ሰጥተዉናል፡፡
(ሐ)ድርጅቱ በአሁኑ ወቅት በተደጋጋሚ የሗላ ታሪክን እንደማይፈትሽ፣ የቀረቡትን መረጃዎች እንደማያረጋግጥ እና ተጠቃሚዎቹ ወንጀል መስራታቸዉን እንደማይፈትሽ እዉቅና ሰጥተዋል፡፡ ማንኛዉንም ዋስትና አለመተላለፍዎን ለማረጋገጥ እና የትኛዉን ዉክልና ሀሰት አለመሆኑን ለይቶ ለማወቅ፣ እኛ በሁሉም አባላት ላይ ምርመራዎችን እና የሗላ ታሪክ ፍተሻ የማድረግ መብታችን የተጠበቀ ነዉ፡፡ ድርጅቱ ይህን መሰሉን ምርመራዎችን እንዲያካሄድ እርስዎ ፈቃድ ሰጥተዋል እና እርስዎ ማንኛዉንም ዋስትና ከጣሱ ወይም እርስዎ የሰጡት ዉክልና ሀሰት ሆኖ ከተገኘ ድርጅቱ አባልነት መከልከል እና/ወይም አባልነትዎን የማቋረጥ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡

2.4 የደንበኝነት ምዝገባ እቅዶች እና ክፍያዎች

የደንበኝነት ምዝገባ እቅዶች እና ተጓዳኝ ክፍያዎቻቸዉ በ "አባልነትዎን ከፍ ያድርጉ" ገጽ ላይ ይገኛሉ፡፡ እነዚህ የደንበኝነት ክፍያዎች ለዉጥ ሊደረግባቸዉ ይችላል፣ ለዉጦቹም ቀደም ተብሎ በተጠቀሰዉ ድረገጽ ላይ የሚለጠፋ ይሆናል፡፡ ከደንበኝነት ክፍያ ጋር በተያያዘ በመስተዳድሮች መካከል ልዩነቶች ሊኖሩ ይችላሉ፣ እነዚህ ልዩነቶችም ለተወሰነ አስተዳደር እና ለዚህ አስተዳደር ተገቢ የሆኑ የንግድ ሁኔታዎች ተግባራዊ የሚሆኑ የክፍያ ዋጋዎችን ያንጸባርቃሉ፡፡

2.5 ከክፍያ ነጻ ሙከራዎች እና ሌሎች የማስታወቂያ ስጦታዎች

ክፍያ የሚጠይቁ አገልግሎቶችን በነጻ መጠቀም የሚያስችሉ ማንኛዉም ከክፍያ ነጻ ሙከራ ወይም ሌላ የማስታወቂያ ስጦታዎች በተጠቀሰዉ የሙከራ ጊዜ ዉስጥ ጥቅም ላይ መዋል አለባቸዉ፡፡

2.6 ክፍያ

(ሀ)ምንም እንኳን የተወሰኑ አገልግሎቶችን ከክፍያ ነጻ ማግኘት ቢቻልም፣ ክፍያ የሚጠይቁ አገልግሎቶች ማግኘት የሚችሉት ስራ ላይ የሚዉል የደንበኝነት ምዝገባ ለፈጻሙ አባላት ወይም በሌላ መልኩ የተጠየቀዉ ክፍያ ሲፈጸም ብቻ መሆኑን እዉቅና ሰጥተዋል፡፡ የደንበኝነት ምዝገባ እና የተከፈለባቸው አገልግሎቶችን በተጠቀሰዉ የክፍያ ዋጋ፣ ለተጠቀሰዉ የጊዜ ቆይታ እና አባልነት ከፍ ማድረግ ገጽ ወይም በተገቢ የግዢ ገጽ ላይ በተጠቀሱት የክፍያ ዘዴዎች አማካኝነት ማግኘት ይቻላል፡፡ የክፍያ ዋጋዎች አባልነት ከፍ ማድረግ ገጽ ላይ በሚታዩት ምንዛሬዎች ተገልጸዋል፣ በሌላ መልኩ ካልተገለጸ በስተቀር ሁሉም ተግባራዊ የሚሆኑ ታክሶችን ያካትታሉ፡፡
(ለ)የእርስዎ አባልነት ወይም የተከፈለባቸው አገልግሎቶች እራስ-በራስ የሚታደስ ይሆናል፡፡ እርስዎ የእራስ-በራስ እድሳቱን በየትኛዉ ጊዜ ላይ ማስቆም ይችላሉ፡፡ የእራስ-በራስ እድሳቱን እና ግዢውን ካላስቆሙ፣ ከዚያ፣ ለተገለጸዉ የጊዜ ቆይታዎች የደንበኝነት ምዝገባዉ እራስ-በራስ የሚታደስ ይሆናል፡፡ በዚህ ድረገጽ የእገዛ ክፍል ዉስጥ የሚገኙትን መመሪያዎች በመከተል የእራሰ-በራስ እድሳቱን ማስቆም ይችላሉ፡፡
(ሐ) እርስዎ ለመረጡት የደንበኝነት ምዝገባ እቅድ ወይም ለመረጧቸው የተከፈለባቸው አገልግሎቶች ተግባራዊ የሚሆኑ የደንበኝነት ምዝገባ ክፍያዎች እኛ የተደጋጋሚ ክፍያ ማስተላለፍ አቅርቦቶች የምንሰጥ ሆኖ ሲገኝ፣ እነዚህን ክፍያዎች ተደጋጋሚነት ባለዉ መልኩ (ምክንያታዊ በሆነ ጊዜ ቆይታ ዉስጥ) ድርጅቱ እንዲቆርጥ እዚህ ላይ ስልጣን ሰጥተዋል፡፡ በእነዚህ ሁኔታዎች ላይ፣ ይህን መሰሉ ስልጣን መቋረጡን የሚገልጽ ከእርስዎ በኩል የጽሁፍ ማሳወቂያ ሲቀርብ፣ ድርጅቱ ክፍያዎችን መቁረጡን ያቆማል፡፡ ማንኛዉም ይህን መሰሉ ማሳወቂያ ድርጅቱ ምክንያታዊ በሆነ ጊዜ ላይ እርምጃ መዉሰድ ከመቻሉ በፊት የተፈፀሙ ክፍያዎችን አይመለከትም፡፡ በማንኛዉም ሁኔታ፣ የደንበኝነት ክፍያዎች በትክክል መቆረጥ እንዲችሉ እርስዎ ወቅታዊ የሆነ፣ የተሟላ እና ትክክለኛ መረጃዎችን ማቅረብ አለብዎት፣ እነዚህም መረጃዎች በየጊዜዉ ሊዘምኑ ይገባል፡፡
(መ)የእኛ የደንበኝነት ምዝገባ ወይም የተከፈለባቸው አገልግሎቶች ክፍያ ዋጋ ላይ በየትኛዉም ጊዜ ላይ ለዉጥ ልናደርግ እንችላለን፡፡ አዲሱ የክፍያ ዋጋ ስራ ላይ የሚዉለዉ እኛ በድረገጻችን ላይ ስለ አዲሱ የክፍያ ዋጋ ዝረዝር መረጃ ከለጠፍን በሗላ እርስዎ ለአዲስ የደንበኝነት ምዝገባ (የእርስዎ የመጀመሪያ የደንበኝነት ምዝገባ ቢሆንም ባይሆንም) ወይም ለተከፈለባቸው አገልግሎቶች ግዢ የሚያመለክቱ ከሆነ ነዉ፡፡ ቀደም ብለዉ የተደረጉ የደንበኝነት ክፍያዎች የእራስ-በራስ እድሳቶች በድሮዉ የክፍያ ዋጋ የሚቀጥሉ ይሆናል፡፡
(ሠ)አጠራጣሪ የክፍያ ማስተላለፍ እንቅስቃሴዎች በሚታዩበት ሁኔታ ላይ፣ እኛ ለጊዜያዊነት ወይም በቋሚነት በእርስዎ ክሬዲት ካርድ የሚተላለፍ ክፍያን ማገድ እና/ወይም ይህን መሰሉን ያልተለመደ እንቅስቃሴ ለማሳወቅ እና/ወይም ተጨማሪ መረጃን ለማግኘት እርስዎን፣ ባንክዎን ወይም ሌላ ተገቢ የሆነ ሶስተኛ አካልን የማነጋገር መብታችን የተጠበቀ ነዉ፡፡

2.7 የክፍያ አገልግሎት አጠቃቀም መመሪያ

የሶስተኛ ወገን የክፍያ አስተላላፊ አገልግሎቶችን በሚጠቀሙበት ወቅት፣ የእነዚህን የክፍያ አስተላላፊ አገልግሎቶች የአጠቃቀም መመሪያን መቀበል እና መከተል ይኖርብዎታል፡፡

2.8 የወርቅ፣ ፕላቲኒየም እና ዳይመንድ አባልነቶች ድንጋጌዎች እና፣ ሳንቲሞች

እባክዎ ከፋይ ገዥዎች በወርቅ፣ ፕላቲኒየምና ዳይመንድ አባላቶች እንደሚከፋፈሉ ይወቁ። የፕላቲኒየምና ዳይመንድ ተጠቃሚዎች ብቻ የተሻሻለ መጣመሪያ፣ መልዕክቶችን መተርጎሚያና በፍለጋ ውጤቶች ላይ እጥፍ ቦታዎችን ይጠቀማሉ እንዲሁም ከተካተቱት ነጻ ሳንቲሞች ይጠቀማሉ። የዳይመንድ ተጠቃሚዎች ብቻ የመልዕክት ቅድሚያን፣ ቅድሚያ ድጋፍን እና በፍለጋ ውጤቶች ላይ የግል መረጃዎቻቸውን ማድመቂያን መጠቀም ይችላሉ።

ስፓርኮች እንደ የቨርቹዋል ስጦታዎችን መላክ ለመሳሰሉ የተከፈለባቸው አገልግሎቶች ለመክፈል ያገለግላሉ፡፡ ጥቅም ላይ የማይውሉ ሳንቲሞች ከተገዙበት ቀን ከ365 ቀናት በኋላ አገል3ግሎታቸው ያበቃል፡፡

2.9 የይለፍ ቃል ደህንነት

የአባልነት ምዝገባ ሂደቱ አካል ስለሆነ፣ የይለፍ ቃል እንዲመርጡ ይጠየቃሉ፡፡ በቀላሉ ሊገመት የማይችል የይለፍ ቃል የመምረጥ እና የይለፍ ቃልዎን ደህንነት የመጠበቀ ሀላፊነቱ የእርስዎ ነዉ፣ እና የእርስዎን ይህን ድረገጽ የመጠቀም ወይም የመመልከት ፈቃድዎን ለሌላ ሶስተኛ ወገን ላለማስተላለፍ ወይም ላለመሸጥ ተስማምተዋል፡፡ የእርስዎ መለያ ደህንነት ላይ ጥርጣሬ እንዲያድርብዎት የሚያደርግ ምክንያት አለ ብለዉ ካመኑ፣ ወዲያዉኑ ሰለ ጉዳዩ እኛን ሊያሳዉቁን እና ጊዜ ሳያጠፋ የእርስዎን መለያ መረጃ በማዘመን የይለፍ ቃልዎን መቀየር አለብዎት፡፡

2.10 የማንነት ማረጋገጫ

እኛ ከጊዜ ወደ ጊዜ ማንነትዎን ለማረጋገጥ መታወቂያ እንዲያቀርቡ ልንጠይቅ እንችላለን:

(ሀ) የእርስዎ ማንነት፤
(ለ) በእርስዎ የቀረበዉ መረጃ፤
(ሐ) የእርስዎ የክፍያ መፈጸሚያ ወይም የክፍያ ማስተላለፊያ መረጃ፤ እና/ወይም
(መ) ለእኛ የአጠቃቀም መመሪያ የእርስዎ ተገዢነት፡፡

3. አገልግሎቱ

አገልግሎቱ ጓደኝነት ወይም የፍቅር ግንኙነት ሊፈልጉ በሚችሉ ወይም በማይፈልጉ አባላት መካከል ግንኙነትን የሚያመቻች የኢንተርኔት መረጃ አገልግሎት ነዉ፡፡ አገልግሎቱ የጋብቻ አደራዳሪ አገልግሎት አይደለም፣ የመልእክት ትዕዛዝ የሙሽራ አገልግሎት ወይም ለፍቅር ግንኙነት የሚያዛምድ አገልግሎት አይደለም፡፡ ድርጅቱ ማንኛዉንም ሌላ አባል ወይም አባላት ከእርስዎ ጋር የማደራደር ምንም አይነት ግዴታ የለበትም፡፡

4. የአገልግሎቱ አጠቃቀም

4.1 በእራስዎ ሀላፊነት

የእርስዎ ይህን አገልግሎት እና ድረገጽ መጠቀም ሀላፊነት የእርስዎ ብቻ መሆኑን እዉቅና ሰጥተዋል፡፡

4.2 ትክክለኛ መረጃ

ለአገልግሎቱ፣ ለድረገጹ እና ለድርጅቱ የሚያቀርቡት መረጃ/ዎች እና ፎቶግራፍ/ፎች በሁሉም መልኩ ትክክለኛ መሆናቸዉን፣ ይህንን ዉል የማይጥሱ እና በሌላ ማንኛዉም ግለሰብ ላይ በምንም መልኩ ጉዳት የማያደርሱ መሆናቸዉን እርስዎ ዉክልና፣ ዋስትና ሰጥተዋል እና ግዴታዎን እንደተወጡ አረጋግጠዋል፡፡

ከላይ የተጠቀሰዉ ላይ ገደብ ሳያስቀምጥ፣ በእኛ ድረገጽ ላይ ማንኛዉም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የያዘ ምስል ማስተላለፍ ወይም መለጠፍ የለብዎትም:

ከእርስዎ ዉጪ የሆነ የማንኛዉንም ግለሰብ ምስል፤
እርቃን ሰዉነት የሚያሳይ፤
እርስዎ የማይታዩበት የሌሎች ነገሮች ምስል፤
የካርቱን ወይም የገለጻ ምስል (ምንም እንኳን እርስዎ ቢሆኑም)፡፡

4.3 ምስጢራዊነቱ ያልተጠበቀ መረጃ

በእርስዎ የቀረበ ማንኛዉም አቅርቦት ወይም መረጃ፣ ይህም የግል መረጃ (በእኛ የግላዊነት መግለጫ ላይ ተለይቶ እንደተቀመጠዉ እና የእርስዎን ሙሉ ስም፣ ፓስታ ሳጥን ቁጥር፣ የስልክ ቁጥር የመሳሰሉትን ሊያካትት የሚችል) ሊያካትት ይችላል፣ ሚስጥራዊነቱ ያልተጠበቀ እና ባለቤት-የሌለዉ ተደርጎ እንደሚወሰድ እና እኛ ይህን መሰሉን አቅርቦት ወይም መረጃ ያለ ምንም ገደብ፣ ይህን አይነቱ የእርስዎ የግል መረጃ አጠቃቀም የእኛን የግላዊነት መግለጫ እና ማንኛዉም አይነት ተግባራዊ ህጎችን የተከተለ እስከሆነ ድረስ መጠቀም እንደምንችል ተስማምተዋል፡፡ በተለይ፣ ድርጅቱ የእርስዎን የመለያ መግለጫ ወደ ሌላ ባለቤትነቱ እና እንቅስቃሴዎቹን የሚቆጣጠረዉ ድርጅቱ ወደ ሆነ ተገቢ የፍቅር ግንኙነት ማፈላለጊያ ድረገጽ ለመቅዳት የእርስዎን አቅርቦት ወይም መረጃ (ይህም ማንኛዉንም መረጃ፣ ፎቶግራፎች፣ ቪዲዬ ወይ የድምጽ ቅጂ) እንዲጠቀም ፍቃድ መስጠትዎን አረጋግጠዋል፡፡ በእርስዎ የቀረበ ማንኛዉም ይህን መሰሉ አቅርቦት እና መረጃ ለሌሎች የዚህ ድረገጽ አባላት እና ተጠቃሚዎች ምልከታ እንደሚቀርብ እዉቅና ሰጥተዋል፡፡

4.4 በዉጪ ሀገር ለምልከታ የሚቀርብ መረጃ

(ሀ) እርስዎ ለእኛ ያቀረቡት ማንናኛም የመለያ መግለጫ መረጃ በእርስዎ የመለያ መግለጫ ላይ በህዝብ መታየት እንዲችል ለምልከታ ክፍት ይሆናል፣ ይህም የተመልካቹን የመገኛ አድራሻ ግምት ዉስጥ የሚያስገባ አይሆንም፡፡ የመለያ መግለጫ በመፍጠር፣ በዉጪ ሀገር የሚገኙ ተቀባዮች የእርስዎን የመለያ መግለጫ መመልከት እንደሚችሉ እዉቅና ሰጥተዋል፡፡
(ለ)ድርጅቱ ዓለም አቀፍ በሆነ መልኩ የእርስዎን የግል መረጃ ለማስቀመጥ ሰርቨሮችን ይጠቀማል፣ እነዚህም እርስዎ ከሚገኙበት ሀገር ዉጪ የሚገኙ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
(ሐ) ድርጅቱ ዓለም አቀፍ በሆነ መልኩ በግለሰቦች ላይ የሗላ ታሪክ እና የወንጀል ታሪክ ፍተሻ ለማድረግ የሥራ ተቋራጮችን ይጠቀማል፣ እነዚህም እርስዎ ከሚገኙበት ሀገር ዉጪ የሚገኙ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
(መ) የደንበኞች አገልግሎት ለመስጠት፣ የቢሮ ስራዎችን ለማከናወን፣ ማጭበርበር መከላከል ተግባራትን ለማከናወን ወይም ለእርስዎ አገልግሎቶችን ለማቅረብ ለእኛ ሰራተኞች ወይም አቅራቢዎች (መገኛ አድራሻቸዉ ወይም አቅርቦቶቻቸዉ እርስዎ ከሚገኙበት ሀገር ዉጪ ሊሆን ይችላል) የግል መረጃዎን እንዲመለከቱ ፍቃድ ልንሰጣቸዉ እንችላለን፡፡

(ሠ) በእነዚህ መመሪያዎች አንቀጽ 4.4(ሀ) እስከ 4.4(መ) ድረስ እና በእኛ የግላዊነት መግለጫ ላይ በጥልቀት ለማሳየት እንደተሞከረዉ፣ በዚህም ይህን መሰሉ አባላት፣ ተቀጣሪዎች እና ሶስተኛ ወገኖች እርስዎ ከሚገኙበት ሀገር ዉጪ የሆኑ፣ ይህን መሰሉ የመረጃ ማስተላለፍ እና ማስቀመጥ የሚፈጥረዉን ስጋት በሙሉ ግንዛቤ እና ተቀባይነት፣ በተለይም ይህን መሰሉ ሀገራት እርስዎ ከሚኖሩበት ሀገር ጋር ተመሳሳይ ወይም ተመሳሳይ ደረጃ የሆነ ጥበቃ የሌላቸዉ መሆኑን ተገንዝበዉ የግል መረጃዎ ለእኛ አባላት፣ ተቀጣሪዎች እና ሶስተኛ ወገኖች መተላለፍ እና መቀመጥ ሁኔታ ላይ በግልጽ ፍቃድዎን ሰጥተዋል፡፡ ሁሉም ማስተላለፎች በእኛ የግላዊነት መግለጫ ዉሎች መሰረት በ Cupid Media የሚመቻቹ ይሆናል፡፡ በእኛ የግላዊነት መግለጫ ዉስጥ በተቀመጠዉ አካሄድ መሰረት እርስዎ የሰጡትን ፈቃድ በየትኛዉም ጊዜ ላይ የመሰረዝ፣ ወይም የግል መረጃዎ ጥቅም ላይ መዋልን መቃወም መብት አለዎት፡፡

4.5 የተመደበ የቅጂ መብት

በእርስዎ ለድርጅቱ በቀረበ ማንኛዉም አቅርቦት ወይም መረጃ ዉስጥ በቀጥታ የሚገኝ ሁሉም የቅጂ መብት በዚህ የአጠቃቀም መመሪያ ወሰን ስር ለድርጅቱ ይመደባል፡፡ እርስዎ በሌላ ግለሰብ ወይም አካል ባለቤትነት የተያዘ ማንኛዉንም አቅርቦት ወይም መረጃ አይለጥፋም፣ አያስተላልፋም ወይም በሌላ መልኩ አያቀርቡም እና ሁሉም በእርስዎ የቀረቡት አቅርቦቶች እና መረጃዎች መነሻነታቸዉ የእራስዎ የሆኑ ስራዎች እና ከሌላ ሶስተኛ ወገን ያልተወሰዱ መሆናቸዉን ዋስትና ሰጥተዋል፡፡

4.6 ህጋዊ ምልከታ

የእርስዎ ድረገጹን እና አገልግሎቱን መጠቀም ህግን የሚጥሱ ወይም እርስዎ ላይ ተፈጻሚ በሚሆኑ ህጎች የተከለከሉ አለመሆናቸዉን ማረጋገጥ አለብዎት፡፡ በየትኛዉም ተግባራዊ በሚሆን ህግ የእርስዎ እርምጃ ህጋዊ መሆኑን የማረጋገጥ የእርስዎ ብቻ ሀላፊነት ነዉ፡፡

4.7 ለቫይረሶች ተጋላጭነት

እርስዎ ድረገጹን ለመመልከት የተከተሉት ሂደት እርስዎን ለቫይረሶች፣ ችግር ያለባቸዉ የኮምፒዉተር ኮድ ወይም ሌሎች የእርስዎን የኮምፒዉተር ስርዓት ሊያበላሹ የሚችሉ ጣልቃ ገብነት አደጋ የማያጋልጥዎ መሆኑን ለማረጋገጥ የእራስዎን ጥንቃቄ ማድረግ ይጠበቅቦታል፡፡ ጥርጣሬዎችን ለማስቀረት፣ አገልግሎቱን፣ ድረገጹን እና ሌላ የተያያዘ ድረገጽ ሲጠቀሙ የሚፈጠር ማንኛዉም ጣልቃ ገብነት ወይም ብልሽት ሀላፊነት አንወስድም፡፡

4.8 የመለያ መግለጫ ይዘት

(ሀ)የእርስዎ መለያ መግለጫ፣ መልእክቶች፣ ቪዲዬዎች እና የድምጽ ቅጂዎች እና እርስዎ ወደ አገልግሎቱ የሚጭኑት ወይም የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ለሆነ ሌላ አባል የሚያስተላልፋት ማንኛዉም አቅርቦት ይዘትን በተመለከተ እርስዎ ብቻዎን ሀላፊነት ይወስዳሉ፡፡
(ለ)በእርስዎ የመለያ መግለጫ ላይ ወይም ድረገጹ ላይ እርስዎ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ይዘቶች እንደማይጭኑ እና እንደማይለጥፋ ተስማምተዋል:

(i)አላግባብ ጥቅም ላይ የዋለ፣ ጸያፍ፣ ልቅ፣ ስድብ፣ ወሲባዊ የሆነ፣ የሚያስፈራራ፣ የሚተነኩስ፣ ዘር የሚሳደብ፣ ተገቢ ያልሆነ ወይም በሌላ መልኩ በእኛ ብቻ በሚታወቅ ሁኔታ ተገቢ ያልሆነ ይዘት፤ ወይም
(ii) ከእርስዎ ሌላ የሆነ ግለሰብን የሚስል፣ የሚገልጽ፣ ለይቶ የሚያሳዉቅ ወይም የሚያስመስል ይዘት፡፡

4.9 ከአባላቶች ጋር የሚደረግ ግንኙነት

የአገልግሎት ተጠቃሚ የሆኑ አባላት ጋር ለሚያደርጉት ግንኙነት እርስዎ ብቻዎን ሀላፊነት ይወስዳሉ፡፡

4.10 አሉታዊ ስምምነቶች

እርስዎ ከዚህ በታች ላለዉ ሁኔታ ዉክልና፣ ዋስትና እና ስምምነት አድርገዋል:

(ሀ) በአገልግሎቱ አማካኝነት ለእርስዎ የቀረበ ማንኛዉንም መረጃ ለእርስዎ መረጃዉን ያቀረበዉ ግለሰብ ቀደም ብሎ ፈቃድ ካልሰጠዎት በስተቀር ይፋ ማድረግ አይችሉም፤
(ለ) እርስዎ ማንኛዉንም የትንኮሳ ወይም ጸያፍ የሆነ ባህሪን የሚያሳይ ድርጊት ላይ አገልግሎቱን በመጠቀም መሳተፍ አይችሉም፣ ይህም የሚያካትታቸዉ የሚከተሉትን ሲሆን በእነዚህ ብቻ ግን አይገደብም: ማንኛዉም ወሲባዊ እና/ወይም ዘር የሚሳደብ፣ ያለአግባብ የሚጠቀም፣ የሚያስፈራራ፣ ተቀባይነት የሌለዉ፣ ጸያፍ፣ የሚተነኩስ፣ ሀሰተኛ፣ ስም የሚያጠፋ፣ ክብርን የሚነካ ወይም ተቃዉሞ የሚያስነሳ አቅርቦት፣ ማንኛዉም ህጋዊ ያልሆነ ወይም ህግን የሚጥስ አቅርቦት፣ ወይም የሌላ ወገኖችን መብቶች (የሚያካትተዉ፣ በዚህ ብቻ አይገደብም፣ የአእምሮ ፈጠራ ባለቤትነት መብቶች እና ግላዊነት መብቶች) የሚነጥቅ ወይም የሚጥስ አቅርቦትን ማሰራጨት ተግባር ላይ መሳተፍ አይችሉም፤
(ሐ) አገልግሎቱን የቡድን ወሲባዊ እንቅስቃሴ ላይ ለመሳተፍ፣ ወይም ከትዳር-ተጨማሪ መቀራረብ ወይም ግንኙነትን ዓላማ አድራሻ መጠየቅ፣ ወይም ለሴተኛ አዳሪነት ወይም እርስዎ በሚኖሩበት ሀገር ዉስጥ ሕገ ወጥ የሆኑ ሌሎች ማንኛዉም እንቅስቃሴዎች ላይ ለመሳተፍ ጥቅም ላይ ማዋል አይችሉም፤
(መ)ማንኛዉንም ግለሰብ መምሰል ወይም ትክክለኛ እድሜዎን መቀየር ወይም ትክክለኛ የትዳር ሁኔታዎን አለማሳወቅ ወይም በየትኛዉም መልኩ ሀሰተኛ ወይም አሳሳች የሆነ መረጃን በእርስዎ የመለያ መግለጫ ላይ ማስፈር አይችሉም፤
(ሠ)እርስዎ "ስፓም"፣ ተያያዥ ደብዳቤዎችን፣ አላስፈላጊ ኢሜይል፣ ወይም ተቀባይነት የሌለዉ የጥቅል የኢሜል ስርጭትን ለማስተላለፍ ኤሌክትሮኒክ ወይም ሌላ ዘዴዎችን በመጠቀም ከአገልግሎቱ ላይ የሌሎች ተጠቃሚዎችን የኢሜይል አድራሻ መልቀም ወይም ሌላ የመገኛ አድራሻ መረጃን መሰብሰብ አይችሉም፤
(ረ) እርስዎ አገልግሎቱን ወይም ድረገጹን ፈቃድ ላልተሰጠዉ የንግድ ዓላማዎች መጠቀም አይችሉም፤
(ሰ) እርስዎ ምንም ገንዘብ፣ የባንክ አካዉንት ወይም ክሬዲት ካርድ ዝረዝር መረጃ ወይም ሚስጥራዊ የሆነ የንግድ መረጃን ከሌላ ማንኛዉም አባል ወይም የአገልግሎቱ ወይም ድረገጹ ተጠቃሚ መጠየቅ ወይም ለመጠየቅ መሞከር አይችሉም፤
(ሸ) እርስዎ በድረገጹ አማካኝነት ግንኙነት ለፈጠሩት ማንኛዉም ግለሰብ ገንዘብ ወይም የንግድ መረጃ መላክ አይችሉም፡፡ ድርጅቱ በዚህ አይነቱ ባህሪ ምክንያት እርስዎ ላይ ለሚፈጠር ለማንኛዉም ኪሳራ (የገንዘብ ወይም ሌላ) ተጠያቂ አይደለም፡፡ እርስዎ ማንኛዉንም ገንዘብ ለመጠየቅ ወይም የንግድ መረጃ ለማግኘት የሚሞክርን ግለሰብ የደንበኛ ድጋፍን በማግኘት ወይም በአባላት መለያ መግለጫ ላይ በሚገኘዉ "ያለ አግባብ ጥቅም ላይ ማዋል" መተግበሪያ አማካኝነት ሪፓርት ለማድረግ ተስማምተዋል፤
(ቀ) እርስዎ ከማንኛዉም አባል የይለፍ ቃል ለመጠየቅ ወይም ለመጠየቅ መሞከር አይችሉም፤
(በ)እርስዎ የገንዘብ እርዳታ፣ ማስታወቂያ ወይም እቃዎች ወይም አገልግሎቶችን መጠየቂያ ይዘት ያለዉን አቅርቦት ለማሰራጨት፣ ለማስተዋወቅ ወይም በሌላ መልኩ ለማተም አገልግሎቱን መጠቀም አይችሉም፤
(ተ) እርስዎ ግንኙነት እንዲያቆሙ በግልጽ ጥያቄ ላቀረበ ግለሰብ ተደጋጋሚ በሆነ መልኩ ግንኙነት በመፍጠር ማስጨነቅ አይችሉም፤
(ቸ) እርስዎ ቫይረሶች ወይም የኮምፒዉተር ሶፍትዌር ወይም ሀርድዌር ተግባራትን ለመገደብ ወይም ለማጥፋት ታስበዉ የተዘጋጁ ወይም ሌላ የኮምፒዉተር ኮዶች፣ መዝገቦች ወይም ፕሮግራሞችን የያዙ አቅርቦቶችን መለጠፍ ወይም ማስተላለፍ አይችሉም፤
(ነ) እርስዎ በየትኛዉም መልኩ ማንኛዉንም የመገኛ አድራሻ ይህም የሚያካትተዉ ገደብ ሳይኖርበት፣ የኢሜል አድራሻዎች፣ የስልክ ቁጥሮች፣ የፈጣን መልእክት መለያዎች፣ የፌስቡክ ተጠቃሚ ስሞች፣ ዩአርኤሎች፣ ወይም ሙሉ ስሞችን ለህዝብ ይፋ በሚሆኑ የእርስዎ መረጃዎች አማካኝነት መለጠፍ ወይም ማስተላለፍ አይችሉም፤
(ኘ) እርስዎ ወደ አገልግሎቱ ለመግባት ሰዉ-ያልሆነ ወይም እራስ-በራስ ቦትስ መጠቀም አይችሉም፤
(አ) ከእኛ የደንበኞች ድጋፍ ተቀጣሪዎች ጋር በስልክ ወይም በሌላ ማንኛዉም ዘዴ ግንኙነት በሚፈጥሩበት ወቅት፣ እርስዎ አገልግሎቱን ያለአግባብ ጥቅም ላይ ማዋል፣ ጸያፍ፣ ልቅ፣ ስድብ፣ ወሲባዊ የሆነ፣ የሚያስፈራራ፣ የሚተነኪስ ወይም ዘርን የሚሰድብ ("የሚያስከፋ ድርጊት") ድርጊትን መፈጸም አይችሉም፡፡ በእኛ ብቻ በሚታወቅ መልኩ፣ እርስዎ የሚያስከፋ ድርጊት ላይ የተሳተፋ ከሆነ፣ የእርስዎን አባልነት ወዲያዉኑ የማቋረጥ መብታችን የተጠበቀ ነዉ፣ እና ከእርስዎ ለወሰድነዉ ማንኛዉም የደንበኝነት ምዝገባ ክፍያዎች ለእርስዎ ተመላሽ የሚደረግበት መብት እንደሌልዎት ተስማምተዋል፤
(ከ) የእርስዎ እድሜ ከ 18 ዓመት በላይ ነዉ፡፡ ሁሉም የእኛ ድረገጽ አባላት እድሜያቸዉ ከ 18 ዓመት በላይ እንዲሆን ይጠበቃል፡፡ የእኛ ድርጅት በማንኛዉም አባል እድሜዉ/ዋ ለአቅም አዳም ካልደረሰ ግለሰብ ጋር ለሚፈጸም የሳይበር ወሲብ፣ ወሲባዊ የመልእክት ግንኙነት፣ ወይም የወሲብ ንክኪ ምንም አይነት ትዕግስት የለዉም፡፡ ህገወጥ የሆነ ወይም ተገቢ ያልሆነ ግንኙነት ለአቅም አዳም ካልደረሰ/ች ግለሰብ ጋር እንደተፈፀመ ማሳወቂያ እንደደረሰን፣ ተገቢ ለሆነዉ የህግ አስፈጻሚ ኤጀንሲ ዝረዝር መረጃዎችን ሪፓርት እናደርጋለን፡፡

4.11 የቅጂ መብት መወሰድ ማሳወቂያ

(ሀ)ድርጅቱ የሌሎችን የአእምሮ ፈጠራ ባለቤትነት መብቶችን ያከብራል፡፡ በድረገጹ ላይ የተቀመጠ ይዘት የእርስዎ ወይም የሶስተኛ ወገን ባለቤትነት የሆነ ነዉ ብለዉ የሚጠረጥሩ ከሆነ፣ እና ይዘቱ የእርስዎን የቅጂ መብት ወይም ሌላ የአእምሮ ፈጠራ ባለቤትነት መብትን ወይም ለሶስተኛ ወገን ባለቤትነት የሆነ የአእምሮ ፈጠራ ባለቤትነት መብትን የሚጥስ ወይም በሚጥስ መልኩ ድረገጹ ላይ ተቀምጧል ብለዉ ከጠረጠሩ፣ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መረጃዎችን ለድርጅቱ በማቅረብ እርስዎ ማሳወቂያ ማስገባት ይቸችላሉ:

(i) የእርስዎ የመገኛ መረጃ – አድራሻ፣ የስልክ ቁጥር፣ እና ኢሜይል አድራሻ ያካትታል፤
(ii) የቅጂ መብት ባለቤቱን ወይም ሌላ የአእምሮ ፈጠራ ባለቤት ፍላጎትን የመወከል ስልጣን ያለዉ ግለሰብ ኤሌክትሮኒክ ወይም አካላዊ ፊርማ፤
(iii) ተወሰዷል ተብሎ የታሰበዉ ወይም የተጠረጠረዉ ስራ ወይ ሌላ የአእምሮ ፈጠራ ባለቤትነት ዝርዝር መግለጫ፤
(iv) ተወሰዷል ተብሎ ተጠረጠረዉ አቅርቦት የሚገኝበት ድረገጽ ስም፤
(v) ተወሰዷል ተብሎ ተጠረጠረዉ አቅርቦት በድረገጹ ላይ የቱ ጋር እንደሚገኝ ዝርዝር መግለጫ፤
(vi) ከታች የተዘረዘሩትን የሚገልጽ የእርስዎ መግለጫ:
(ሀ) ጥቅም ላይ የዋለዉ አቅርቦት በቅጂ መብት ባለቤቱ፣ በወኪሉ ወይም በህግ ፈቃድ አለማግኘቱ የእርስዎ ጥሩ እምነት አመለካከት መሆኑን ይገልጻል፤
(l) በእርስዎ ማሳወቂያ ዉስጥ የቀረበዉ መረጃ ትክክል መሆኑን እና በጥሩ እምነት አመለካከት የቀረበ እና እርስዎ የቅጂ መብቱ ባለቤት ወይም የአእምሮ ፈጠራ ባለቤት ወይም በቅጂ መብቱ ባለቤት ወይም የአእምሮ ፈጠራ ባለቤትን ወክለዉ እንዲንቀሳቀሱ የህግ ፈቃድ ያለዎት መሆኑን፣ ሀሰተኛ መረጃ ሆኖ ከተገኘ በህግ እንደሚጠየቁበት እያወቁ መጠያቂዉን ማስገባትዎን ይገልጻል፡፡

ማሳወቂያዎች ሊላኩ የሚችሉት:
AfroIntroductions.com, PO Box 9304፣ Gold Coast MC, QLD 9726, Australia
ኢሜይል: copyright@AfroIntroductions.com

4.12 የምስሎች ጥቅም ላይ መዋል

ከአንቀጽ 4.5 መመሪያዎች በተጨማሪ፣ ለድርጅቱ ማንኛዉም ፎቶግራፎች፣ አቅርቦት፣ መረጃ ወይም ይዘት በማቅረብ፣ ድርጅቱ ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ማድረግ እንደሚችል እዉቅና ሰጥተዋል እና ተስማምተዋል:

(ሀ) ማባዛት፣ መጠቀም፣ መቅዳት፣ ማከናወን፣ ማሳየት፣ ማሰራጨት እና ከአቅርቦቱ፣ መረጃዉ ወይም ይዘት መጠቀም ይችላል፤
(ለ) ይህን መሰል አቅርቦት፣ መረጃ እና ይዘት ላይ የተመሰረቱ ስራዎችን ማዘጋጀት፣ በሌሎች ስራዎች ወይም ሌሎች ሚዲያዎች ዉስጥ መጠቀም ይችላል፤ እና
(ሐ) ከላይ በአንቀጽ 4.12(ሀ) እና 4.12(ለ) ስር ለድርጅቱ የተሰጡትን መብቶች ለሌሎች ፍቃድ መስጠት፣ እና እርስዎ ለማንኛዉም እና ለሆሉም ይህን መሰሉ ጥቅም ላይ መዋል፣ የሚያካትተዉም፣ ያለ ምንም ገደብ፣ ለማንኛዉም የማስታወቂያ ወይም የንግድ ዓላማዎች እንደሚዉል ፍቃድ ሰጥተዋል፡፡ እርስዎ በዚህ አንቀጽ ዉስጥ የተጠቀሰዉን ፍቃድ ለመስጠት ስልጣኑ እንዳለዎት ዋስትና ሰጥተዋል፡፡

4.13 የመልእክት ትዕዛዝ የሙሽሮች ጋብቻዎች

ይህ ድረገጽ "መልእክት ትዕዛዝ ሙሽሮች" የጋብቻ-ማዛመድ አገልግሎቶችን አይሰጥም፣ እናም አገልግሎቱን እንደሚሰጥም መወሰድ የለበትም፣ በየትኛዉም መልኩ፣ አያግዝም፣ አያስማማም፣ አያስተዋዉቅም ወይም ለተጠቃሚዎቹ አያቀርብም፡፡ እርስዎ የሚኖሩበት አስተዳደር የጋብቻ-ማዛመድ አገልግሎቶች ወይም ግለሰቦች ጋብቻ እንዲፈጽሙ ጥያቄ የሚያቀርቡ ማስታወቂያዎችን ሊገድብ እንደሚችል እዉቅና ሰጥተዋል፡፡

እርስዎ የሚገኙት በፊሊፒንስ፣ ቤላሩስ ወይም ነዋሪዎቹ የጋብቻ-ማዛመጃ አገልግሎቶችን የሚከለክል አስተዳደር ዉስጥ ከሆነ፣ የጋብቻ-ማዛመጃን የሚከለክ ህግን ለሚጥስ ማንኛዉም ዓላማዎች አገልግሎቱን ወይም ድረገጹን እንደማይጠቀሙ እዚህ ላይ ዋስትና፣ ዉክልና እና ስምምነት ፈጽመዋል፡፡ የጋብቻ-ማዛመጃ የትኛዉም ክልከላ ላይ ጥሰት እንደማይፈጽሙ ማረጋገጥ ሀላፊነት የእርስዎ ብቻ መሆኑን እዚህ ላይ እዉቅና ሰጥተዋል እና ተስማምተዋል፣ ከዚህም በተጨማሪም በዚህ አንቀጽ 17 ስር ያሉ ማስያዣዎች እርስዎ ለፈጸሙት የትኛዉም የጋብቻ-ማዛመጃ የሚከለክል ህግ ጥሰት ተግባራዊ እንደሚሆኑ እዉቅና ሰጥተዋል እና ተስማምተዋል፡፡

4.14 የድንበር ገደቦች

የድረገጹን እና/ወይም የሞባይል መተግበሪያውን አገልግሎት ከዚህ በታች የተገለጹት ሊጠቀሙት አይችሉም
(i) የኩባ፣ ኢራቅ፣ ሊቢያ፣ ሰሜን ኮርያ፣ ኢራን፣ ሶርያ፣ ቤላሩስ ሪፑብሊክ፣ የሩሲያ ፌደሬሽን፣ በሩሲያ ፌደሬሽን የተያዙ የድንበር ወሰኖች፣ ወይም ማንኛው በዩኤስ እና/ወይም ኢዩ የእቃዎች ማእቀብ የተጣለበት ሌላ አገር ነዋሪዎች፣ ወይም
(ii) ማንኛውም በዩ.ኤስ የግምጃ ቤት መምሪያ ዝርዝር ወይም በዩ.ኤስ የንግድ መምሪያ የትእዛዞች መከልከል ሰንጠረዥ ላይ በልዩ ሁኔታ የተመደበ ዜጋ ተብሎ የተመዘገበ ሰው፡፡
የድረገጹን ወይም የሞባይል መተግበሪያውን አገልግሎት በመጠቀም በየትኛውም እነዚህ አገራት ውስጥ፣ በአገራቱ ቁጥጥር ስር እንደማይገኙ፣ ወይም የአገራቱ ዜጋ ወይም ነዋሪ እንዳልሆኑ፣ ወይም በየትኛውም እንደዚህ አይነቱ መዝገብ ላይ እንዳልተመዘገቡ ያረጋግጣሉ፡፡

5. መረጃ

5.1 መረጃን መቆጣጠር

እኛ የዚህን የአጠቃቀም መመሪያ መስፈርቶችን ማሟላታቸዉን ለማረጋገጥ ሁሉንም የመለያ መግለጫዎችን፣ መልእክቶችን፣ ዉይይት፣ ፈጣን መልእክቶች፣ ቪዲዬዎች እና የድምጽ ቅጂዎችን የመቆጣጠር መብታችን የተጠበቀ ነዉ፡፡ ለእኛ ደንበኞች ከፍተኛ ደረጃ የሆነ አገልግሎትን እና ደህንነቱ የተጠበቀ የኦንላይን አካባቢን ማቅረባችንን ለማረጋገጥ፣ ለእኛ ደንበኞች የኦንላይን ደህንነት ተግባራትን እንዲያቀርቡ አንድ ወይም ሁለት ሶስተኛ ወገኖችን ተሳታፊ አድርገናል፡፡ ይህን ደህንነት ማቅረብ ከእርስዎ ኮምፒዉተር ወይም የእኛን ድረገጽ ለመመልከት የተጠቀሙት መሳሪያ ላይ ግላዊ-ያልሆኑ የተወሰኑ መረጃዎችን መሰብሰብ ይፈልጋል፡፡ ለእርስዎ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ስጋት የሌለበት የኦንላይን አካባቢን ብቻ ዓላማ ያደረገ ምክንያት ግላዊ-ያልሆኑ የተወሰኑ መረጃዎች በቀጥታም ይሁን በሶስተኛ ወገኖች ጥቅም ላይ እንደሚዉሉ፣ እርስዎ እዚህ ላይ በግልጽ እዉቅና ሰጥተዋል እና ተስማምተዋል፡፡ ምንም እንኳን ምንም አይነት ግላዊ መረጃ ባይሰበሰብም፣ እኛ ለደህንነት አገልግሎት የምንቀጥራቸዉ ማንኛዉም ሶስተኛ ወገን ሥራ ተቋራጮች ከፍተኛ የሆነ የመረጃ ጥበቃ እና የግላዊነት መስፈርትን እንደሚከተሉ እናረጋግጣለን፡፡.

5.2 መረጃን ማቀናበር

ምንም እንኳን በአገልግሎቱ አባላቶች የሚለጠፋ ወይም የሚላኩ ሁሉንም መልእክቶች ወይም ሌሎች አቅርቦቶችን እኛ ባንገመግምም ወይም መገምገም ባንችልም፣ እና በእነዚህ መልእክቶች እና አቅርቦቶች ዉስጥ ለሚገኘዉ ይዘት ሀላፊነት ባይኖርብንም፣ ይህን ለማድረግ ምንም አይነት ግዴታዎች ባይኖረንም፣ ይህን የአጠቃቀም መመሪያ የሚጥሱ ወይም በሌላ መልኩ ተቀባይነት የሌላቸዉ መልእክቶች ወይም አቅርቦቶች (ይህም የመለያ መገለጫዎች፣ መልእክቶች፣ ቪዲዮዎች እና የድምጽ ቅጂዎች) የማጥፋት፣ የማንቀሳቀስ ወይም የማቀናበር መብታችን የተጠበቀ ነዉ፡፡

5.3 የመረጃ ደህንነት

በማያስደስት መልኩ፣ በኢንተርኔት አማካኝነት የሚደረግ ምንም ዓይነት የመረጃ ማስተላለፍ ሙሉ በሙሉ ከስጋት ነጻ መሆኑን ማረጋገጥ አይቻልም፡፡ እኛ ይህን መረጃ ለመጠበቅ ጥረት እናደርጋለን፣ በእኛ የግላዊነት መግለጫ መሰረት እርስዎ ለእኛ መረጃ ወይም እኛ ለሌሎች ሶስተኛ ወገኖች የሚተላለፈዉ ማንኛዉም መረጃ ደህንነትን ላይ እኛ ዋስትና እና ደህንነቱ የተጠበቀ መሆኑን አናረጋግጥም፡፡ በዚህም መሰረት፣ እርስዎ ለእኛ የሚያስተላልፋት ማንኛዉም መረጃ በራስዎ ሀላፊነት እንደሚተላለፍ በግልጽ እዉቅና ሰጥተዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪም እኛ የእርስዎን መረጃ ለተፈቀደላቸዉ ሶስተኛ ወገኖች፣ ይህም እርስዎ በሚኖሩበት አስተዳደር ዉስጥ ያሉትንም ሆነ የሌሉትንም ያካትታል፣ በተለይ ደግሞ እርስዎ ከሚኖሩበት ሀገር ጋር ተመሳሳይ ወይም የሚቀራረብ ደረጃ ያለዉ ጥበቃ የሌላቸዉ ሀገሮች ዉስጥም ላሉ ሶስተኛ ወገኖች ማስተላለፋችንን፣ ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚኖረዉን ስጋት ሙሉ በሙሉ በመገንዘብ በግልጽ ፈቃድ ሰጥተዋል፡፡ በእኛ የግላዊነት መግለጫ ዉስጥ በተቀመጠዉ አካሄድ መሰረት በየትኛዉም ጊዜ ፈቃድዎን የመሰረዝ፣ ወይም የእርስዎን የግል መረጃ ጥቅም ላይ ማዋላችንን መቃወም ይችላሉ፡፡

ከላይ የተገለጸዉ ሳይቀየር፣ የእርስዎን ማስተላለፍ እንደደረሰን፣ ይህን መሰሉን መረጃ ደህንነት ለመጠበቅ ምክንያታዊ የሆኑ እርምጃዎችን የምንወስድ ይሆናል፡፡

6. የተገደበ አጠቃቀም

በሌላ መልኩ በጽሁፍ ስምምነት ካላደረግን በስተቀር፣ ድረገጹን እንዲመለከቱ የሚፈቀድልዎት ለግል ጥቅም ብቻ ነዉ፡፡ የንግድ ተቋማት፣ ቡድኖች፣ ድርጅቶች እና ኩባንያዎች አባል ሆነዉ መመዝገብ አይፈቀድላቸዉም፡፡ በሌላ መልኩ በግልጽ ህትመት ካልተከለከለ፣ ለግል ጥቅም በድረገጹ ዉስጥ የሚገኝ ማንኛዉንም መረጃ ቅጂ የማተም ስልጣን ተሰጥትዎታል፡፡

7. ቀጥተኛ ማስታወቂያ

ድርጅቱ ስለ እርስዎ የሚሰበስበዉን የግል መረጃ ለቀጥተኛ ማስታወቂያ ዓላማ ጥቅም ላይ ሊያዉል ወይም ይፋ ሊያደርግ እንደሚችል እርስዎ በግልጽ ፈቃድ ሰጥተዋል፡፡ በእኛ የግላዊነት መግለጫ ዉስጥ በተቀመጠዉ አካሄድ መሰረት በየትኛዉም ጊዜ ፈቃድዎን የመሰረዝ፣ ወይም የእርስዎን የግል መረጃ ጥቅም ላይ ማዋላችንን መቃወም ይችላሉ፡፡

8. ግንኙነት

በአገልግሎቱ ላይ የሚደረጉ ለዉጦች ወይም ጭማሪዎች፣ ወይም በድርጅቱ እና ከድርጅቱ ጋር አብረዉ የሚሰሩ ቢዝነሶች ማንኛዉም ምርት እና አገልግሎቶች በተመለከተ ኤሌክትሮኒክ መልእክቶችን የመላክ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡

9. ማስታወቂያዎች

9.1 ብቸኛ ሀላፊነት

በድረገጹ ላይ (ወደ አስተዋዋቂዎች ድረገጾች የሚወስዱ ሀይፐርሊንኮችንም ያካትታል) የሚታዩ ማስታወቂያዎች (የሚኖሩ ከሆነ) ይዘት ሀላፊነት የአስተዋዋቂዎች ብቻ ነዉ፡፡ ይህን መሰሉ ማስታወቂያዎች መቀመጥ ድርጅቱ የአስተዋዋቂዉን ምርት ወይም አገልግሎት እንዲጠቀሙ መምከሩን ወይም የምርቱ መቀበሉን አያሳይም፡፡ እያንዳንዱ አስተዋዋቂ ከማስታወቂያዎቹ ጋር ተያያዘዉ ለሚነሱ ዉክልናዎች ለብቻዉ ሀላፊነት ይወስዳል፡፡

10. የአእምሮ ፈጠራ ንብረት ባለቤትነት

ድርጅቱ በአገልግሎቱ እና በድረገጹ እና ተያያዝ በሆነዉ የአእምሮ ፈጠራ ንብረት መብቶች ዉስጥ ያሉትን መብቶች፣ ስልጣን፣ እና ፍላጎቶች በሙሉ አሉት እና በግልጽ ያልተጠቀሱትንም መብቶቹ የተጠበቁ ናቸዉ፡፡

10.1 የቅጂ መብት

የዚህ አገልግሎት እና ድረገጽ (ይህም ጽሁፍ፣ ግራፊክስ፣ ሎጎዎች፣ ቁልፎች፣ የድምጽ ቅጂዎች እና ሶፍትዌርን ያካትታል) የቅጂ መብቶች ባለቤትነት እና ፍቃድ ያለዉ ድርጅቱ ነዉ፡፡ በቅጂ መብት ደንብ 1968 (Cth) እና እርስዎ በሚገኙበት አድራሻ ላይ ተፈጻሚ በሚሆኑ ተመሳሳይ ህጎች ስር ላሉት ሁኔታዎች ዓላማ፣ እና ተግባራዊነት ሌላ፣ እና በዚህ የአጠቃቀም መመሪያ በግልጽ ከተሰጠዉ ስልጣን ዉጪ፣ እርስዎ በምንም አይነት መልኩ ወይም ዘዴ:

(ሀ) መቀየር፣ በድጋሚ መፍጠር፣ ማስቀመጥ፣ ማከፋፈል፣ በወረቀት ማተም፣ ማሳየት፣ ማከናወን፣ ለህትመት ማብቃት ወይም ከየትኛዉም የአገልግሎቱ ወይም ድረገጹ ክፍል ላይ የወጣ ስራን መፍጠር አይችሉም፤ ወይም
(ለ) ከየትኛዉም የአገልግሎቱ ወይም ድረገጹ ክፍል ላይ የተገኘ ምንም አይነት መረጃ፣ ምርት እና አገልግሎትን ለንግድ መጠቀም አይችሉም፤

ካለ እኛ ቀድሞ የተሰጠ የጽሁፍ ፍቃድ ዉጪ፡፡

10.2 የንግድ ምልክቶች

በሌላ መልኩ ካልተገለጸ በስተቀር፣ ™ ይም ® ምልክቶች የሰፈሩበት ማንኛዉም ስራ ወይም መሳሪያ ምዝገባ የተደረገበት የንግድ ምልክት ነዉ፡፡ የእኛን እንቅስቃሴዎች፣ ምርቶች ወይም አገልግሎቶችን በመጥቀስ በእኛ ድርጅት ባለቤትነት የሆነ ማንኛዉንም የንግድ ምልክቶችን ከተጠቀሙ፣ የንግድ ምልክቱ የድርጅቱ ባለቤትነት እንደሆነ የሚያሳይ መግለጫ ማካተት አለብዎት፡፡ እርስዎ የእኛን የንግድ ምልክት ሊጠቀሙ የማይፈቀድልዎት ሁኔታዎች:

(ሀ)በእርስዎ የንግድ ምልክቶች ዉስጥ ወይም ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል፤
(ለ) የእኛ ካልሆኑ እንቅስቃሴዎች፣ ምርቶች ወይም አገልግሎቶች ጋር በተያያዘ፤
(ሐ) ግራ በሚያጋባ፣ አሳሳች ወይም አታላይ በሆነ መልኩ፤ ወይም
(መ) እኛን ወይም የእኛን መረጃ፣ ምርቶች ወይም አገልግሎቶች (ይህም የሚያካትተዉ ያለምንም ገደብ፣ አገልግሎቱን እና ድረገጹን) ታማኝነት በሚያሳጣ መልኩ፡፡

11. የተጣመሩ ድረገጾች

11.1 ለእርስዎ እንዲቀል ብቻ የቀረቡ ማጣመሪያዎች

ድረገጹ ወደ ሌሎች ድረገጾች ("የተጣመሩ ድረገጾች") የሚጠቁሙ ማጣመሪያዎች ሊኖሩት ይችላሉ፡፡ እነዚህ ማጣመሪያዎች ነገሮችን ለማቅለል ብቻ የቀረቡ ናቸዉ እና ወቅታዊ ላይሆኑ እና በየጊዜዉ ላይቀየሩ ይችላሉ፡፡ ከተጣመሩ ድረገጾች ጋር ለሚገናኝ ይዘት ወይም የግላዊነት ልምምድ እኛ ሀላፊነት አንወስድም፡፡

11.2 ምንም አይነት ድጋፍ አያሳይም

የእኛ ማጣመሪያዎች ከተጣመሩ ድረገጾች መያያዛቸዉ የተጣመሩ ድረገጾችን ባለቤቶች ወይም አንቀሳቃሾችን፣ ወይም ምንም አይነት መረጃ፣ ግራፊክስ፣ አቅርቦቶች፣ በተጣመሩ ድረገጾች ላይ የተጠቀሱ ወይም የሚገኙ ምርቶች ወይም አገልግሎቶች፣ ከዚህ በተቃራኒ በተቀመጠዉ ሁኔታዎች በስተቀር፣ ድርጅቱ መቀበልን፣ ማረጋገጫ ወይም ምክር መስጠቱን የሚያሳይ ተደርጎ መወሰድ የለበትም፡፡ ከመጠቀምዎ በፊት የተጣመሩ ድረገጾችን የአጠቃቀም መመሪያ እና ግላዊነት መግለጫ እንዲገመግሙ እንመክርዎታለን፡፡

12.የግላዊነት መግለጫ

እኛ የመግለጫዉን ዉሎች ለመከተል ግዴታዎችን እንወጣለን የእኛ ግላዊነት መግለጫ ይህም በድረ ገጹላይ ይገኛል፣ እና ተግባራዊ ለሚሆኑ ህጎች እና ከእኛ እንቅስቃሴዎች ጋር ለመስማማት ከጊዜ ወደ ጊዜ ሊሻሻል ይችላል፡፡

በእኛ ግላዊነት መግለጫ ስር በተቀመጠዉ መሰረት የእርስዎን ግላዊ መረጃ እኛ እንድንሰበስብ፣ እንድናቀናብር እና ጥቅም ላይ እንድናዉል በግልጽ ፈቃድዎን ሰጥተዋል፡፡ በእኛ ግላዊነት መግለጫ ስር በተቀመጠዉ አካሄድ መሰረት፣ በየትኛዉም ጊዜ የእርስዎን ፈቃድ መሰረዝ፣ ወይም የእርስዎ የግል መረጃ ጥቅም ላይ መዋልን መቃወም ይችላሉ፡፡

የግል መረጃን ለማንኛውም ሶስተኛ ወገን አንሸጥም ወይም የግል መረጃን ለማንኛውም የንግድ ዓላማ ቢሆን ለሶስተኛ ወገን አሳልፈን አንሰጥም (ያ የንግድ ዓላማ በግላዊ መግለጫችን ውስጥ የተጠቀሰ ካልሆነ በቀር)።

13. የድረ ገጽ ወይም አገልግሎቶች መሸጥ

ድርጅቱ ድረገጹን፣ አገልግሎቶችን ወይም የንግድ ስራዎቹን (ወይም ከነዚህ ዉስጥ በከፊሉ) ከሸጠ ወይም ድርጅቱን የሚቆጣጠረዉ አካል ላይ ለዉጥ ከተፈጠረ፣ ለእርስዎ አገልግሎቱን ለማቅረብ እና ቀጥተኛ ማስታወቂያ ለማስተላለፍ ዓላማዎች፣ ድርጅቱ የግል መረጃን፣ ልዩ መደብ የግል መረጃ እና እርስዎ በድረገጹ ላይ የሚያስተላልፉትን ማንኛዉም ሌላ መረጃ ወይም አገልግሎቶች (ይህም ፎቶግራፎች እና የእርስዎን ይፋ ሆነ የመለያ መገለጫ) ግዢዉን ለፈጸመዉ ወይም አዲስ ተቆጣጣሪ አካል ወይም ግለሰብ ይፋ ሊያደርግ፣ ሊመድብ ወይም ሊያስተላልፍ እንደሚችል እርስዎ ግልጽ በሆነ መልኩ ፍቃድ ሰጥተዋል፡፡

አዲሱ ገዢ ወይም ተቆጣጣሪ አካል ወይም ግለሰብ እርስዎ ከሚኖሩበት ሀገር ሌላ የሚገኝ መሆኑን ግልጽ በሆነ መልኩ እዉቅና ሰጥተዋል፣ እና እርስዎ ከሚኖሩበት ሀገር ዉጪ የግል መረጃዎ መተላለፋን ፍቃድ ሰጥተዋል፡፡

14. የሀላፊነት ማስተባበያ እና የተጠያቂነት ገደብ

14.1 በአዉስትራሊያ የተጠቃሚዎች ህግ ስር የተጠቃሚዎች መብቶች

በአዉስትራሊያ አስተዳደር ዉስጥ የሚገኙ ግለሰቦች፣ በአዉስትራሊያ የተጠቃሚዎች ህግ (ኤሲኤል) ስር የተወሰኑ መብቶች እና የማስተካከያ አካሄዶች አልዎት፡፡

14.2 ምርቶችን እና አገልግሎቶችን ለግል፣ ቤት ዉስጥ ወይም ለቤተሰብ ጥቅም ሲዉል የሚሰጡ ዋስትናዎች

በአዉስትራሊያ አስተዳደር ዉስጥ እኛ ለግል፣ ለቤት ዉስጥ ወይም ለቤተሰብ ጥቅም ላይ የሚዉል ምርቶች ወይም አገልግሎቶችን በምናቀርብበት ጊዜ ላይ፣ በኤሲኤል የሚቀርቡት የተጠቃሚዎች ዋስትናዎች በምንም አይነት ሁኔታ አይገደቡም ወይም ከተግባራዊነት ዉጪ አይሆኑም፡፡

14.3 ለግል፣ ለቤት ዉስጥ ወይም ለቤተሰብ ጥቅም ላይ የሚዉል ምርቶች ወይም አገልግሎቶች የሚሰጡ ዋስትናዎች

በአዉስትራሊያ አስተዳደር ዉስጥ እና ለግል፣ ለቤት ዉስጥ ወይም ለቤተሰብ ጥቅም ላይ የማይዉሉ ምርቶች ወይም አገልግሎቶችን በምናቀርብበት ጊዜ ላይ፣ ሆኖም ግን ዋጋቸዉ ከ $40,000 በታች ሲሆኑ የተጠቃሚዎች ዋስትናዎች ቀጥሎ ለተጠቀሱት የተገደቡ ይሆናል:

(ሀ) ምርቶች በሚሆኑበት ሁኔታ ላይ:

(i) የምርቶቹ ቅያሬ ወይም ተለዋጭ የሆነ ምርት ማቅረብ፤
(ii) ይህን መሰሉ ምርቶች ላይ ጥገና፤
(iii) ይህን መሰሎቹን ምርቶች ቅያሬ ወይም ተለዋጭ ምርቶች ክፍያ፤ ወይም
(iv) የተጠገኑት ምርቶች ወጪ ክፍያዎች፤ እና

(ለ) አገልግሎቶች በሚሆኑበት ሁኔታ ላይ:

(i) አገልግሎቱን በድጋሚ ማቅረብ፤ ወይም
(ii) አገልግሎቱን በድጋሚ የማቅረብ ወጪ ክፍያ፡፡

14.4 ለትክክለኛነት ምንም ዋስትና የለም

በአንቀጽ 14.2 እና 14.3 በመገዛት፣ እኛ በአገልግሎቱ ወይም በድረገጹ (ይህም በድርጅቱ ወይም በሌላ ማንኛዉም ግለሰብ ወይም አካል የተሰቀለ ወይም የተሰራጨ የአባላት መለያ መገለጫ፣ ምክር፣ አስተያየት፣ መግለጫ ወይም ሌላ የሚታይ መረጃን ያካትታል) አማካኝነት የቀረበ አቅርቦት ወይም አገልግሎት የሚታመን፣ ትክክለኛ ወይም የተሟላ ወይም የእርስዎ የአገልግሎቱ ወይም የድረገጹ ምልከታ የማይቆራረጥ፣ ጊዜዉን የጠበቀ ወይም ደህንነቱ የተጠበቀ መሆኑ ላይ ምንም አይነት ዉክልና ወይም ዋስትናዎችን አንሰጥም፡፡ በአገልግሎቱ ወይም በድረገጹ አማካኝነት የቀረበ መረጃ ወይም አቅርቦት ላይ በመንተራስ በተወሰደ እርምጃ ወይም በመረጃዉ ላይ መመርኮዝ ምክንያት እርስዎ ላይ ለሚደርስ ምንም አይነት ኪሳራ እኛ ተጠያቂ አንሆንም፡፡ በዚህ ድረገጽ ላይ በሚታይ መረጃ ወይም አቅርቦት ላይ በመንተራስ ወይም በመመርኮዝ እርምጃ ከመዉሰድዎ በፊት የእራስዎን ምርመራዎች ማድረግ ይጠበቅብዎታል፡፡ በማንኛዉም ይህን መሰሉ አቅርቦት ወይም መረጃ ላይ የሚያደርጉት ምርኮዛ የእራስዎ ሀላፊነት ብቻ መሆኑን እርስዎ እዉቅና ሰጥተዋል፡፡

14.5 የአገልግሎቶች መገኘት ላይ ምንም ዋስትና የለም

በአንቀጽ 14.2 እና 14.3 በመገዛት፣ አገልግሎቱ ወይም ድረገጹ የማይቆራረጥ ወይም ከስህተት-የነጻ መሆኑን ዋስትና አንሰጥም፡፡ አገልግሎቱ በ "እንዳለዉ ሁኔታ" መሰረት ይሰራጫል፡፡ በአገልግሎቶች ወይም ድረገጹ መገኘት ላይ መዘግየቶች፣ ክፍተቶች፣ እና መቆራረጦች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ህግ በሚፈቅደዉ ሁኔታ ላይ፣ አገልግሎቱ (የድረገጹ መገኘት) ያለምንም አይነት ዋስትና፣ በግልጽ የሰፈረም ሆነ ወይም ለመጠቆም የተሞከረ፣ ይህም የሚያካትተዉ ነገር ግን በዚህ ብቻ አይገደብም ለተወሰነ ዓላማ የሚዉል ለመጠቆም የተሞከረ የመሸጥ አቅም እና አቋም ዋስትናዎች ሳይሰጡ አገልግሎቶቹ እንደሚቀርቡ እርስዎ እዉቅና ሰጥተዋል፡፡

14.6 ለመጠቆም የተሞከሩት ዋስትናዎች የማያካትቱት

ህግ በሚፈቅደዉ ሁኔታዎች እና አንቀጽ 14.2 እና 14.3 ላይ በመገዛት፣ በዚህ የአጠቃቀም መመሪያ ዉስጥ ለመጠቆም የተሞከሩ ማንኛዉም አይነት ሁኔታዎች ወይም ዋስትናዎች እዚህ ላይ አይካተቱም፡፡ ህጉ የትኛዉንም ሁኔታ ወይም ዋስትና ሲጠቁም፣ እና ይህ ህግ ምንም አይነት ሁኔታዎች ወይም ዋስትናንን በሚጠቁምበት ሁኔታ ላይ፣ እና ይህ ህግ የዚህን መሰሉ ሁኔታዎች ወይም ዋስትናዎች ተግባራዊነት፣ ወይም የእኛን ተጠያቂነት ላለማካተት ወይም ላለመቀየር ክልከላ ሲጥልብን፣ ይህ ሁኔታ ወይም ዋስትና እንደተካተተ ተደርጎ ይወሰዳል ነገር ግን ከዚህ ቀጥሎ የተጠቀሱት የሁኔታ ወይም ዋስትና ጥሰት ላይ ብቻ የእኛ ተጠያቂነት የሚገደብ ይሆናል:

(ሀ) ጥሰቱ ከምርቶች ጋር የተያያዘ ከሆነ:

(i) ለምርቶቹ ቅያሪ መስጠት ወይም ተመሳሳይ ምርቶች ማቅረብ፤
(ii) እነዚህን ምርቶች መጠገን፤
(iii) ምርቶቹን የመቀየር ወይም ተመሳሳይ ምርቶችን የማግኘት ወጪ ክፍያ፤ ወይም
(iv) ምርቶቹን የመጠገን ወጪ ክፍያ፤ እና

(ለ) ጥሰቱ ከአገልግሎቶች ጋር የተያያዘ ከሆነ:

(i) አገልግሎቶቹን በድጋሚ ማቅረብ፤ ወይም
(ii) አገልግሎቶቹን በድጋሚ የማቅረብ ወጪ ክፍያ

14.7 ለኪሳራ ምንም አይነት ተጠያቂነት የለም

እርስዎ አገልግሎቱን፣ ድረገጹን ወይም የተጣመሩ ድረገጾች ሲጠቀሙ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በየትኛዉም ምክንያት ይከሰት (ይህም ግድየለሽነትንም ያካትታል) ለሚያጋጥምዎት ለማንኛዉም ኪሳራ ወይም ብልሽት ተጠያቂ አይደለንም፣ እንዲሁም ከእርስዎ አጠቃቀም፣ በዚህ አገልግሎት ወይም ድረገጽ ዉስጥ የሚገኝ ወይም መመልከት የሚቻል መረጃ ላይ መመርኮዝ ለሚመጣ ማንኛዉም ኪሳራ እኛ ተጠያቂ አንሆንም፡፡ ጥርጣሬዎችን ለማስቀረት እና ቀጥሎ የተጠቀሱትን ሁኔታዎች አጠቃላይነት ሳይገድብ:

(ሀ)ከእርስዎ አገልግሎቱን ወይም ድረገጹን ከመጠቀም ወይም ለመጠቀም ከመዘግየት ወይም አለመቻል፣ ወይም ከአገልግሎቱ ወይም ድረገጹ የተገኘ መረጃ፣ ምርት እና ሌሎች አገልግሎቶች፣ ወይም በሌላ መልኩ ድረገጹን ከመጠቀም የሚመነጭ፣ በዉሉ መሰረት ቢሆንም፣ ግድ የለሽነት ወይም ሌላ ጥሰት፣ ጥብቅ የሆነ ተጠያቂነት ወይም ሌላ መልክ ያለዉ፣ ምንም እንኳን ድርጅቱ ይህን መሰሉ ጉዳት ሊደርስ እንደሚችል ቀደም ብሎ ምክር የሰጠ ቢሆንም እንኳን ከእነዚህ ጋር በየትኛዉም መንገድ የተያያዙ ቀጥተኛ፣ ተዘዋዋሪ፣ ልዩ ወይም ተከታታይ ለሆነ ጉዳቶች ድርጅቱ ምንም አይነት ሀላፊነት ወይም ተጠያቂነትን አይቀበልም፤
(ለ) እርስዎ ለአገልግሎቱ ወይም ድረገጹ ለሚያቀርቡት ማንኛዉም መረጃ ድርጅቱ ምንም አይነት ሀላፊነት ወይም ተጠያቂነትን አይቀበልም እንዲሁም እርስዎ ያቀረቡት ማንኛዉም መረጃ ወይም አቅርቦት በሌሎች አባላቶች ወይም ተጠቃሚዎች ጥቅም ላይ ቢዉል ወይም ያለ አግባብ ጥቅም ላይ ቢዉል ድርጅቱ ምንም አይነት ሀላፊነትን አንወስድም፤
(ሐ) የማንኛዉም አባል ወይም የአገልግሎቱ ሌላ ተጠቃሚ ባህሪ፣ ይህም ያለ ገደብ የሚያካትተዉ ማንኛዉም ግለሰብ ላይ አካላዊ ጉዳት የሚያደርስ ባህሪንም ያካትታል ድርጅቱ ሀላፊነት ወይም ተጠያቂነትን አይቀበልም፡፡

15. የኦንላይን የፍቅር ግንኙነትን የሚመለከት የተለየ ማስጠንቀቂያ

15.1 ስጋቶች

በኦንላይን የፍቅር ግንኙነት ላይ ስጋቶች እንዳሉ እዉቅና ሰጥተዋል፣ ይህም ያለገደብ የሚያካትታቸዉ፣ ባለማወቅ እድሜዉ/ዋ ለአቅመ አዳም ካልደረሰ ወይም በሀሰተኛ ማስመሰያ ወይም ለወንጀል ዓላማ ከሚንቀሳቀስ ግለሰብ ጋር ሊተዋወቁ እንደሚችሉ እዉቅና ሰጥተዋል፡፡ ከሌሎች ተጠቃሚዎች ጋር ግንኙነት ሲፈጥሩ ወይም በአካል ሲገናኙ፣ በተለይ ደግሞ በአካል ለመገናኘት ከወሰኑ ሁሉንም አስፈላጊ የሆኑ ጥንቃቄዎችን ለመዉሰድ ተስማምተዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪም፣ አገልግሎቱን መጠቀም ከመጀመርዎ በፊት የእኛን የኦንላይን ፍቅር ግንኙነት ደህንነት ምክሮችን ለመገምገም ተስማምተዋል፡፡

15.2 የአባላትን ማንነት በተመለከተ ምንም ዋስትና የለም

ኢንተርኔት ላይ የተጠቃሚዎችን ማንነት ማረጋገጥ እጅግ አስቸጋሪ መሆኑን እዉቅና ሰጥተዋል፡፡ እያንዳንዱ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ አባላት እና ተጠቃሚዎች ማንነታችን ነዉ ብለዉ ያቀረቡት መረጃ ትክክል ነዉ በማለት ድርጅቱ ዋስትና መስጠት አይችልም እናም አይሰጥም፡፡ ከዚህም በመቀጠል፣ የአባላት የመለያ መገለጫዎች ታማኝ፣ ትክክለኛ እና የተሟላ መሆኑን ድርጅቱ ዋስትና መስጠት አይችልም እናም አይሰጥም፡፡ በዚህም መሰረት፣ ከዚህ አገልግሎት ወይም ድረገጽ ሌሎች አባላቶች ጋር የሚያደርጓቸዉ ግንኙነቶች ላይ እርስዎ ጥንቃቄ መዉሰድ አለብዎት፡፡

16. አገልግሎት ማቋረጥ

16.1 ለአባላት ተፈጻሚ የሚሆን ዉል

የዚህ አገልግሎት አባል እስከሆኑ ወይም በሌላ መልኩ ድረገጹን እስከተጠቀሙ ድረስ ይህ ዉል በሙሉ ሀይል እና ተግባሩ ይጸናል፡፡

16.2 በእርስዎ አማካኝነት አባልነትን ማቋረጥ

እኛ የእርስዎን አባልነትን ማቋረጥ የጽሁፍ ማሳወቂያ እንደደረሰን እርስዎ አባልነትዎን በየትኛዉም ጊዜ፣ ለማንኛዉም ምክንያት አባልነትንዎን ማቋረጥ ይችላሉ፡፡ የአባልነት ማቋረጥ ማሳወቂያ በዚህ ድረገጽ እኛን ያግኙን ክፍል ዉስጥ ወደሚገኘዉ አድራሻ በመላክ፣ በዚህ ድረገጽ እኛን ያግኙን ክፍል ዉስጥ ወደሚገኘዉ የኢሜይል አድራሻ፣ ወይም በድረገጹ አባላት ክፍል ዉስጥ የሚገኘዉን አባልነትን አጥፋ ሊንክ በመጫን መላክ ይቻላል፡፡ የእርስዎን አባልነት በማቋረጥዎ ምክንያት የአባልነት ምዝገባ ክፍያዎችዎ ተመላሽ እንዲሆኑ አያደርግም፡፡

16.3 ለተወሰኑ የዩናይትድ ስቴትስ ነዋሪዎች የተሰጠ ልዩ አባልነትን የማቋረጥ መብት

እርስዎ የደንበኝነት ምዝገባዎን በሚፈጽሙበት ወቅት የአሪዞና፣ ካሊፎርኒያ፣ ኬነቲከት፣ ኤሊኖይስ፣ አዮዋ፣ ሚኒሶታ፣ ኒዉ ዮርክ፣ ኖርዝ ካሮሊና፣ ኦሀዮ ወይም ዊስኮንሰን ነዋሪ ከነበሩ፣ ከዚህ ቀጥሎ ያሉት ድንጋጌዎች እርስዎ ላይ ተፈጻሚ ይሆናሉ:

(ሀ) ክፍያ ለሚከፈልባቸዉ አገልግሎቶች ክፍያ በፈጸሙ ባሉት (3) የስራ ቀናቶች (ማቋረጥ የሚቻልበት ጊዜ ቆይታ) ዉስጥ በየትኛዉም ጊዜ ላይ ይህን ዉል፣ ያለምንም ቅጣት ወይም ግዴታ ማቋረጥ ይችላሉ፡፡ ይህን ዉል ለማቋረጥ፣ እርሰዎ ይህን ዉል ሊያቋርጡ እንደሆነ፣ ወይም ይህን የሚያመላክት መግለጫ ሀሳብ ያለዉ ፊርማ እና ቀን ያረፈበት የመልእክት ማሳወቂያ ሊልኩልን ይገባል፡፡ ይህ ማሳወቂያ ሊላክ የሚገባዉ ለ: AfroIntroductions.com, ማሳሰቢያ: ክፍያ ማስመለስ ማሳወቂያ፣ PO Box 9304, Gold Coast MC, QLD 9726, Australia፡፡ ማቋረጥ በሚቻልበት ጊዜ ቆይታ ዉስጥ እርስዎ ማሳወቂያዉን መላክ ወይም ማድረስ ከቻሉ፣ በተጠቀሰዉ ጊዜ ዉስጥ፣ ድርጅቱ በዚህ ድንጋጌ ዉስጥ ተገዢ የሚሆኑ እርስዎ የፈጸሟቸዉ ማናቸዉንም ክፍያዎች የሚመልስ ይሆናል፡፡

የደንበኝነት ምዝገባዎን በሚያፈጽሙበት ወቅት እርስዎ የካሊፎርኒያ፣ ኢሊዮንስ፣ ኒዉ ዮርክ፣ ወይም ኦሃዮ ነዋሪ የሆኑ ከሆነ፣ ከዚህ ቀጥለዉ የተጠቀሱት ድንጋጌዎች እርስዎ ላይ ተፈጻሚ ይሆናሉ:

(ለ) የደንበኝነት ምዝገባዉ ጊዜ ቆይታዉ ሳያበቃ ለህልፈተ ህይወት በሚዳረጉበት ሁኔታ ላይ፣ እርስዎ በሞት ከተለዩበት ጊዜ በሗላ ላለዉ የጊዜ ቆይታ ሊመደብ የሚችል እርስዎ የፈጸሙት ክፍያ የተወሰነ ከፍል ወደ እርስዎ ሀብት ተመላሽ የሚሆንበት መብት አለዎት፡፡ የእርስዎ የደንበኝነት ምዝገባ ክፍያ ጊዜ ቆይታ ከማብቃቱ በፊት፣ እርስዎ በከፋ ሁኔታ አካል ጉዳተኛ የሚሆኑ ከሆነ (ድረገጹን ለመጠቀም የማይችሉ ከሆነ)፣ እርስዎ አካል ጉዳተኛ ከሆኑበት ጊዜ በሗላ ላለዉ የጊዜ ቆይታ ሊመደብ የሚችል እርስዎ የፈጸሙት ክፍያ የተወሰነ ከፍል ተመላሽ የሚሆንበት መብት አለዎት ይህንንም ለማድረግ በሚከተለዉ አድራሻ ለድርጅቱ ማሳወቂያ በማቅረብ አለብዎት: AfroIntroductions.com, ማሳሰቢያ: ክፍያ ማስመለስ ማሳወቂያ፣ PO Box 9304፣ Gold Coast MC, QLD 9726, Australia

16.4 የእርስዎን አገልግሎቱን የማግኘት ሁኔታ ማቋረጥ

እኛ፣ በእኛ ፍጹም የሆነ ዉሳኔ፣ የእርሰዎን የአገልግሎቱን ሁሉንም ወይም በከፊል የማግኘት ሁኔታን አሳዉቀን ወይም ሳናሳዉቅ፣ ለማንኛዉም ምክንያት፣ ይህም ያለገደብ የሚያካትታቸዉ፣ ማንኛዉም የማጭበርበር፣ ያለአግባብ ጥቅም ላይ ማዋል፣ ወይም በሌላ መልኩ ህገ ወጥ እንቅስቃሴ፣ ወይም በሌላ መልኩ ሌሎች ተጠቃሚዎች በአገልግሎቱ እንዳይረኩ የሚያደርግ ምክንያቶች በየትኛዉም ጊዜ ላይ ልንገድብ፣ ልናቋርጥ ወይም ልናግድ እንችላለን፡፡

16.5 በእኛ በኩል አባልነትን ማቋረጥ

እርስዎ ይህንን ስምምነት መጣስዎን እኛ ለይተን ካወቅን (በእኛ ፍጹም የሆነ ዉሳኔ) ወዲያዉኑ የእርስዎን አባልነት እና አገልግሎቱን የማግኘት ሁኔታ ልናቋርጥ እንችላለን፡፡ የማቋረጥ ማሳወቂያ እርስዎ ለመጨረሻ ጊዜ ለእኛ ባቀረቡት የኢሜይል አድራሻ ይላክልዎታል፡፡ ከእርስዎ አባልነት ጋር በተያያዘ በድርጅቱ የወጣ ወጪ ወይም የደረሰ ኪሳራን ቀንሰን ከማቋረጥ በሗላ ለነበሩ ተገቢ የሆኑ ወቅቶች አስቀድሞ-የተከፈሉ ማንኛዉም ክፍያዎችን ለእርስዎ ተመላሽ ይደረጋሉ፡፡

16.6 ጥቅም ላይ-ባለማዋል ምክንያት አገልግሎት እንዳይሰጥ ማድረግ

እርስዎ አገልግሎት ላይ የሚዉል የተከፈለበት የደንበኝነት ምዝገባ ከሌለዎት በስተቀር አገልግሎቱን ለተከታታይ 6 ወራቶች ካልተጠቀሙት የድረገጽ መለያዎን አገልግሎት እንዳይሰጥ ልናደርግ እንችላለን፡፡

16.7 በተጠቃሚ ውሎች (መረጃ፣ መሰረዝ እና ተጨማሪ ክፍያዎች) ደንቦች2013 ስር የሚደረግ ማቋረጥ

ይህ ክፍል እርስዎ በተጠቃሚ ውሎች (መረጃ፣ መሰረዝ እና ተጨማሪ ክፍያዎች) ደንብ 2013 ("ደንቦች") ስር በተገለጸው መሰረት "ተጠቃሚ" ከሆኑ እና የዩኬ ነዋሪ ሆነው አገልግሎቱን መጠቀም ካልጀመሩ ብቻ በእርስዎ ላይ ተፈጻሚ ይሆናል። ደንቦቹ በእነዚህ የአጠቃቀም ድንጋጌዎች ላይ ተፈጻሚ በሚሆኑበት ጊዜ ለአገልግሎቱ በአባልነት በተመዘገቡ በአስራ አራት (14) ቀናት ውስጥ የጽሁፍ ማስታወቂያ በመስጠት አባልነትዎን ሊያቋርጡ ይችላሉ። አገልግሎቱን በአባልነት እንደተመዘገቡ ወዲያውኑ ሊጠቀሙ ይችላሉ።

(ሀ) አገልግሎቱን መጠቀም ካልጀመሩ የእርስዎ የማቋረጥ ማሳወቂያ እኛ ጋር ከመድረሱ በፊት በነበሩት 14 ቀናቶች ዉስጥ የፈጸሙት ክፍያ ይመለስልዎታል፡፡ ከዚህ ቀጥሎ ከተጠቀሱት ድርጊቶች ማንኛዉንም ካከናወኑ የእርስዎ የክፍያ ማስመለስ መብቶች ተፈጻሚነት አይኖራቸዉም:

(i) መልእክቶችን ለአባላቶች መላክ፤
(ii) ከአባላቶች የተላኩ መልእክቶችን ማንበብ፤
(iii) ፍላጎት አሳይ ማሳወቂያዎችን ለአባላቶች መላክ፡፡

16.8 በሸማቾች መብቶች መመሪያ 2011/83/EU (CRD) መሰረት የሚደረግ ማቋረጥ

ይህ ክፍል እርስዎ በሸማቾች መብቶች መመሪያ 2011/83/EU ("ደንቦች") ፍቺ ስር የሚመደቡ "ሸማች" ከሆኑ እና በአውሮፓ ሕብረት ውስጥ ነዋሪ ከሆኑ እና አገልግሎቱን መጠቀም ካልጀመሩ ብቻ በእርስዎ ላይ ተፈጻሚ ይሆናል። ደንቦቹ በእነዚህ የአጠቃቀም ድንጋጌዎች ላይ ተፈጻሚ በሚሆኑበት ሁኔታ ለአገልግሎቱ አባልነት በተመዘገቡ በአስራ አራት (14) ቀናት ውስጥ የጽሁፍ ማስታወቂያ በመስጠት አባልነትዎን ማቋረጥ ይችላሉ። አገልግሎቱን በአባልነት ከተመዘገቡ በኋላ ወዲያውኑ ሊጠቀሙ ይችላሉ።

(a) በሸማቾች መብቶች መመሪያ 2011/83/EU መሰረት በተሰጡዎ በአስራ አራት (14) ቀናት የመሰረዣ ጊዜ ውስጥ አገልግሎቶቹን መጠቀም ጀምረው ከሆነ አገልግሎቱን እንድናቀርብልዎ ጥያቄ ማቅረብ ይኖርብዎታል። አገልግሎቱን እንድናቀርብልዎ ጥያቄ አቅርበው ከሆነ አገልግሎቱን እስከሰረዙበት ጊዜ ድረስ ለቀረበልዎ አገልግሎት መክፈል ይኖርብዎታል። የሚከተሉትን በማድረግ አገልግሎቱን ማግኘት ወደመጀመር ይወሰዳሉ፡

(i) ለአባላት መልዕክት በመላክ፣
(ii) ከአባላት የተላኩ መልዕክቶችን በማንበብ፣
(iii) ለአባላት የግንኙነት ፍላጎት መግለጫ በመላክ።

(b) በሸማቾች መብቶች መመሪያ 2011/83/EU መሰረት በተሰጡዎ በአስራ አራት (14) ቀናት የመሰረዣ ጊዜ ውስጥ አገልግሎቶቹን መጠቀም ካልጀመሩ የማቋረጫ ማስታወቂያ ለእኛ በሚደርስበት በ14 ቀናት ውስጥ ለከፈሉት ለየትኛውም ክፍያ ተመላሽ ይሰጥዎታል።

17. ካሳ

በህግ እስከተፈቀደዉ መጠን፣ ድርጅቱን፣ ተባባሪዎች፣ የኮርፓሬሽን ተያያዝ አካሎች፣ ባለድርሻ አካላት፣ ኦፊሰሮች፣ ተቀጣሪዎች፣ ኤጀንቶች እና ተወካዮችን ከዚህ ቀጥሎ በተጠቀሱት ምክንያት ለሚፈጠሩ ከማንኛዉም እና ከሁሉም ይግባኞች፣ ኪሳረዎች፣ ጉዳት፣ ታክስ (ጂኤስቲ ያካትታል)፣ ተጠያቂነቶች እና/ወይም ድርጅቱን፣ ተባባሪዎች፣ የኮርፓሬሽን ተያያዥ አካሎች፣ ባለድርሻ አካላት፣ ኦፊሰሮች፣ ተቀጣሪዎች፣ ኤጀንቶች እና ተወካዮች ለሚሸፈን ወጪዎች (ይህም በሙሉ ካሳ መሰረት የህግ ወጪዎችን ያካትታል) ፣ ካሳ ለመክፈል፣ ለመከላከል ተስማምተዋል:

(ሀ) በእርስዎ የተፈጸመ ማንኛዉም የእነዚህ ዉሎች ጥሰት፤
(ለ) ከእርስዎ ጋር ሊተሳሰር ወይም ሊያያዝ የሚችል ማንኛዉም ያልተፈቀደ የዚህ ድረገጽ አጠቃቀም፡፡
(ሐ) በእርስዎ የተፈጸመ ማንኛዉም የህግ ጥሰት፣ እና
(መ) ከዚህ ድረገጽ ጋር በተያያዘ እርስዎ የሚፈጽሙት እርምጃ ወይም ያልወሰዱት እርምጃ፡፡

ለማንኛዉም የይገባኛል ጥያቄ መከላከያ ለመስጠት ያልተጓደለ ትብብርን ለማድረግ ተስማምተዋል፡፡ እኛ ለማንኛዉም ጉዳዮች፣ በሌላ በኩል ካሳ የሚያስፈልገዉ ጉዳይ፣ ለዚህ ይገባኛል ጥያቄ ተጠያቂ ሆነዉ እስከቀረቡ ድረስ ብቻችንን መከላከያ እና ቁጥጥር ለማድረግ መብታችን (ነገር ግን ይህን ለማድረግ ግዴታ የለብንም) የተጠበቀ ነዉ፡፡

18. አጠቃላይ

18.1 ለዉሎች አለመገዛት

ከእኛ ምክንያታዊ ቁጥጥር ዉጪ በሆኑ ሁኔታዎች ምክንያት ለእነዚህ የአጠቃቀም መመሪያዎች መገዛት ካልተቻለ ድርጅቱ ለማንኛዉም የዉሎች አለመገዛት ተጠያቂ አይሆንም፡፡

18.2 ምንም አይነት ማንሻ የለም

በአንድ አጋጣሚ በዚህ የአጠቃቀም መመሪያ ዉስጥ ያሉ ማንኛዉም የእኛን መብቶች ካነሳን፣ እነዚህ መብቶች በሌላ ማንኛዉም አጋጣሚ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ይነሳሉ ማለት አይደለም፡፡

18.3 የተናጠል ተግባራዊነት

ከዚህ የአጠቃቀም መመሪያ ዉስጥ ማናቸዉም ዉሎች በማንኛዉም ምክንያት ስራ ላይ የማይዉሉ፣ ሊተገበሩ የማይችሉ ወይም ህግን የጣሱ ተደርገዉ ቢወሰዱ፣ የተቀሩት የአጠቃቀም መመሪያ ዉሎች ተግባራዊነታቸዉ ይቀጥላል፡፡

18.4 የስምምነቱ ቋንቋ

ይህ ስምምነት የሚጠቀመዉ ቋንቋ እንግሊዝኛ ነዉ፡፡ ድርጅቱ በእንግሊዝኛ ቋንቋ የሆነዉን ስምምነት በእርስዎ ቋንቋ ተርጉሞ ሲያቀርብ እርስዎ ለመረዳት እንዲቀልዎ ብቻ መሆኑን ተስማምተዋል፡፡ በእንግሊዝኛ ቋንቋ የሆነዉን ስምምነት እና በተተረጎመዉ መካከል ልዩነቶች ቢፈጠሩ፣ በእንግሊዝኛ ቋንቋ የሆነዉ ይህ ስምምነት ስራ ላይ የሚዉል ይሆናል፡፡

18.5 ለዉጦች

እኛ እነዚህን የአጠቃቀም መመሪያዎች የማሻሻል መብታችን የተተበቀ ነዉ፡፡ ማሻሻያዎች በድረገጹ ላይ ማሳወቂያ እንደተደረገባቸዉ ስራ ላይ የሚዉሉ ይሆናል፡፡ ይህን መሰሉን ማሳወቂያ ተከትሎ የእርስዎ ቀጣይነት ያለዉ የዚህ ድረገጽ መጠቀም በእነዚህ የአጠቃቀም መመሪያዎች ለመገዛት እርስዎ መስማማትዎን የሚገልጹ ይሆናል፡፡

18.6 ዉክልና

በዚህ ስምምነት ዉስጥ የሚገኙ ወይም አገልግሎቱን ወይም ድረገጹን የሚመለከቱ ማንኛዉንም የእርስዎ መብቶችን ለየትኛዉም ሶስተኛ ወገን በዉክልና መስጠት አይችሉም፡፡ ድርጅቱ በዚህ ስምምነት ዉስጥ የሚገኙ ወይም አገልግሎቱን የሚመለከቱ ማንኛዉንም ወይም ሁሉንም መብቶች እና ግዴታዎችን ለማንኛዉም ሶስተኛ ወገን በዉክልና መስጠት ይችላል፡፡ ድርጅቱ በሚፈልግበት ወቅት፣ በዚህ ስምምነት ዉስጥ የሚገኙ የድርጅቱ ግዴታዎች በሌላ ሶስተኛ ወገን ሲወሰዱ፣ ድርጅቱ በዚህ ስምምነት ስራ ከሚገኙ ከማንኛዉም እና ከሁሉም ተጠያቂነቶች ነጻ ነዉ፡፡

18.7 ግንኙነት

በዚህ ስምምነት እና በእርስዎ አገልግሎቱን ወይም ድረገጹን መጠቀም ምክንያት በእርስዎ እና በድርጅቱ መካከል ምንም አይነት የንገድ ሽርክና፣ አጋርነት፣ ቅጥር፣ ወይም የኤጀንሲ ግንኙነት እንደሌለ ተስማምተዋል፡፡

18.8 የሚገዛ ህግ

(ሀ) በአዉሮፓ ሕብረት ዉስጥ በሚገኝ ሀገር ዉስጥ ያሉ ተጠቃሚዎች ይህ ስምምነት በእንግሊዝ እና ዌልስ ዉስጥ ስራ ላይ በሚል ህጎች የሚገዛ መሆኑን እና የዚህ አስተዳደር ፍርድቤቶች ብቻ ለሆነዉ አስተዳደር ለመገዛት ተስማምተዋል፡፡
(ለ) በአዉሮፓ ሕብረት ዉስጥ በማይገኝ ሀገር ዉስጥ ያሉ ተጠቃሚዎች ይህ ስምምነት በኪዉንስላንድ፣አዉስትራሊያ ህጎች የሚገዛ መሆኑን እና የዚህ አስተዳደር ፍርድቤቶች ብቻ ለሆነዉ አስተዳደር ለመገዛት ተስማምተዋል፡፡

19. ትርጓሜዎች

በዚህ የአጠቃቀም መመሪያ ዉስጥ፣ የሚከተሉት አገላለጾች ተጓዳኝ ትርጓሜ አላቸዉ:

"ይግባኝ" ማለት፣ ከግለሰብ ጋር በተያያዘ፣ ይግባኝ፣ ጥያቄ፣ ማስተካከያ፣ ክስ፣ ጉዳት፣ ብልሽት፣ ኪሳራ፣ ወጪ፣ ተጠያቂነት፣ እርምጃ፣ አካሄድ፣ የእርምጃ ትክክለኝነት፣ የካሳ ይገባኛል ወይም ገንዘብ ተመላሽ ማድረግ ወይም በግለሰቡ ላይ ወይም በግለሰቡ ሊከሰት ወይም ሊደረግ ወይም እንደገና ሊወሰድ የተፈለገ፣ በየትኛዉም መልኩ የተነሳ እና የተረጋገጠም ወይም ያልተረጋገጠ፣ ወይም አሁኑኑ፣ ለወደፊቱ ወይም ሊከሰት ይችላል ተብሎ የሚጠበቅ ተጠያቂነት ነዉ፡፡

"ለንግድ መጠቀም"ማለት ለንግድ መጠቀም፣ ለገበያ ማቅረብ፣ ማስተዋወቅ፣ ማበልጸግ፣ ማስተሳሰር፣ ጥናት ማድረግ፣ መሸጥ እና ለትርፍ ወይም ለጥቅም ሌላ ማንኛዉንም እንቅስቃሴ ማድረግ ነዉ፡፡

"ኩባንያ" ማለት Cupid Media Pty Ltd (ACN 104 844 564)፣ በኒው ሳውዝ ዌልስ፣ አውስትራሊያ ውስጥ የተመዘገበ ኩባንያ ማለት ሲሆን ይህም የትኛውንም ከCupid Media Pty Ltd

"አዉሮፓ ሕብረት" ማለት የአዉሮፓ ሕብረት ተብለዉ የሚታወቁት በአዉሮፓ ዉስጥ የሚገኙ መንግስታት የፓለቲካ እና የኢኮኖሚ ህብረት ነዉ፡፡

"በአዉሮፓ ሕብረት ዉስጥ የሚገኝ ሀገር" ማለት ማንኛዉም የአዉሮፓ ሕብረት ወቅታዊ አባል የሆነ እና የስምምነቶቹ ወገን የሆነ ሀገር ነዉ እና ማለት አዉስትራሊያ፣ ቤልጂየም፣ ቡልጋሪያ፣ ክሮሺያ፣ ሳይፕረስ፣ ቼክ ሪፐብሊክ፣ ዴንማርክ፣ ኢስቶኒያ፣ ፊንላንድ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ግሪክ፣ ሀንጋሪ፣ አየርላንድ፣ ጣሊያን፣ ላቲቪያ፣ ሊቱኒያ፣ ሉክሰምበርግ፣ ማልታ፣ ሆላንድ፣ ፓላንድ፣ ፓርቹጋል፣ ሮማኒያ፣ ስሎቫኪያ፣ ስሎቬኒያ፣ ስፔይን፣ እና ስዊድን ናቸዉ፡፡

"የግል መረጃ" ማለት ማንኛዉም ተለይቶ የሚታወቅ ተፈጥሯዊ ግለሰብ ('መረጃዉ የሚመለከተዉ') ጋር ተያያዥነት ያለዉ ማንኛዉም መረጃ ነዉ፤ ተለይቶ የሚታወቅ ተፈጥሯዊ ግለሰብ ማለት ሊለይ የሚችል፣ በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ፣ በተለይ ደግሞ መለያ በሆኑ ለምሳሌ ስም፣ የመለያ ቁጥር፣ የመገኛ መረጃ፣ የኦንላይን መለያ ወይም የተፈጥሯዊዉን ግለሰብ አካላዊ፣ ፊዚዮሎጂካል፣ የዘር፣ አእምሯዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ባህላዊ ወይም የማህበረሰብ መለያ የሚመለከቱ አንድ ወይም ከዚያ በላይ ምክንያቶች መሰረት ሊለይ የሚችል ግለሰብ ነዉ፡፡

"ክፍያ የሚጠይቁ አገልግሎቶች"ማለት ስራ ላይ የሚዉል የደንበኝነት ምዝገባ ላደረጉ ክፍያ-የሚፈጽሙ አባላቶች የሚቀርቡ አቅርቦቶች እና አገልግሎቶች ማለት ነዉ፡፡

"የግላዊነት መግለጫ" ማለት በድረገጹ ላይ የቀረበዉ የድርጅቱ የግላዊነት ፓሊሲ ነዉ፡፡

"አገልግሎት" ማለት በድረገጹ አማካኝነት ለአባላት ጥቅም የቀረቡ አቅርቦቶች ነዉ፡፡

"ልዩ መደብ የግል መረጃ" ማለት የዘር ወይም ብሄር መነሻ፣ ፓለቲካዊ አቋሞች፣ ሀይማኖታዊ ወይም የፍልስፍና እምነቶች፣ የንግድ ማህበር አባልነት፣ የእርስዎ የወንጀል መዝገቦች፣ የዘር እና ልዩ በሆነ መልኩ ተፈጥሯዊ ግለሰብን ለመለየት የሚዉል ባዮሜትሪክ መረጃ፣ ጤንነትዎን የሚመለከት መረጃ ወይም የወሲብ ህይወትዎን ወይም ወሲባዊ አቋምን የሚመለከት መረጃን የሚገልጽ የግል መረጃ ነዉ፤

"ድረገጽ" ማለት ባለቤትነቱ እና እንቅስቃሴዎቹ የሚከናወኑት በዚህ ድርጅት የሆነዉ ይህ ድረገጽ ነዉ፡፡

"የአጠቃቀም መመሪያ" ማለት በድርጅት ከጊዜ ወደ ጊዜ የሚሻሻሉ በእርስዎ እና በድርጅቱ መካከል የሚደረገዉን ስምምነትን የሚፈጥሩ እነዚህ የአጠቃቀም መመሪያዎች ናቸዉ፡፡

"እኛ"፣ እና "የእኛ" ሁሉም ድርጅቱን ይወክላል፡፡