የግላዊነት መግለጫ

1. Cupid Media የግላዊነት መግለጫ

(ለመጨረሻ ጊዜ ወቅታዊ የተደረገበት ቀን 4 ጃኑዋሪ 2024)

1. የመጀመሪያ

(a) አጠቃላይ

AfroIntroductions.com (የ ድረገጽ) በ Cupid Media Pty Ltd ACN 104 844 564፣ በአውስትራሊያ የተመዘገበ ኩባንያ ባለቤትነት ስር የሚሰራ ድረገጽ ነው። (Cupid Media)።

Cupid Media የተጠቃሚውን ግላዊነት ለማስጠበቅ በትጋት ይሰራል። የድረገጻችን ጎብኚዎችና ተጠቃሚዎች የግላዊነታቸው መጠበቅ እና የየትኛውም የሚያቀርቡት የግል መረጃቸው/ ዳታቸው ሚስጥራዊነትና ደህንነት እንደሚያሳስባቸው እንገነዘባለን።

የግል መረጃ የምንቀበለው፣ የምንጠቀመውና ይፋ የምናደርገው በዚህ የግላዊነት መግለጫና የግል ዳታ በምንሰበስብበት ግዛት ውስጥ ተፈጻሚነት ባላቸው ህጎች መሰረት ብቻ ነው። በዚህ የግላዊነት መግለጫ እና በተፈጻሚ ህግ መካከል የትኛውም አለመጣጠም የሚፈጠር ከሆነ እንደ የትኛውም ያለመጣጣም መጠን ላይ ተመስርቶ ተገቢው ህግ ተፈጻሚነት ይኖረዋል።

(ለ) ግንኙነት

የግንኙነት አድራሻ ዝርዝሮቻችን የሚከተሉት ናቸው:

የኦንላይን/ኢንተርኔት ድጋፍ ቅጽ: ጽዚህ ጋር ይጫኑ (ይህን አማራጭ ለፈጣን አገልግሎት ይጠቀሙ)

ኢሜይል: team@AfroIntroductions.com

ስልክ ቁጥር: +61 7 5571 1181

የፋክስ ቁጥር: +61 7 3103 4000

ፖስታ: AfroIntroductions.com, PO Box 9304, Gold Coast MC, QLD 9726, Australia

ዳይሬክተር: Kristina Sakunts, William Alena

የግላዊነት ጉዳዮች የኢሜይል አድራሻ: privacy@cupidmedia.com

ነዋሪነትዎ በአውሮፓ ሕብረት ውስጥ ከሆነ VeraSafe ለዳታ ጥበቃ ጉዳዮች የ Cupid Media’ የአውሮፓ ሕብረት ተወካይ ተደርጎ ተሾሟል። ከላይ የተገለጸውን የግንኙነት መረጃችንን በመጠቀም ከእኛ ጋር ግንኙነት ከማድረግ በተጨማሪ ከVeraSafe ጋር የግል መረጃዎን ከማሰናዳት ሂደት ጋር ተያያዥነት ባላቸው ጉዳዮች ላይ ግንኙነት ማድረግ ይቻላል። እንደዚህ አይነት ጥያቄ ለመጠየቅ ይህን የግንኙነት ቅጽ፡ https://www.verasafe.com/privacy-services/contact-article-27-representative.

በመጠቀም ከ VeraSafe ጋር ግንኙነት ያድርጉ።

በአማራጭነት ከVeraSafe በሚከተሉት አድራሻዎች ግንኙነት ማድረግ ይቻላል፡

ስም: VeraSafe Czech Republic s.r.o
አድራሻ: Klimentsk6 46 Prague 1, 11002 Czech Republic፣ ወይም

ስም: VeraSafe Ireland Ltd
አድራሻ: Unit 3D North Point House, North Point Business Park, New Mallow Road, Cork T23AT2P, Ireland.

መኖሪያዎ ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ከሆነ VeraSafe በዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላላ የዳታ ጥበቃ ደንብ አንቀጽ 27 መሰረት በዩናይት ኪንግደም ውስጥ Cupid Media ተወካይ ሆኖ ተሾሟል። ከላይ የተገለጸውን የግንኙነት መረጃ በመጠቀም ከእኛ ጋር ግንኙነት ከማድረግ በተጨማሪ ከVeraSafe ጋር ከእርስዎ የግል መረጃ /ዳታ/ አጠቃቀም ጋር ተያያዥነት ባላቸው ጉዳዮች ላይ ግንኙነት ማድረግ ይችላሉ። ይህን ጥያቄ ለማቅረብ እባክዎ VeraSafeን ይህን የግንኙነት ቅጽ በመጠቀም: https://verasafe.com/public-resources/contact-data-protection-representative ወይም በስልክ ቁጥር +44 (20) 4532 2003 ያነጋግሩ።

በአማራጭነት ከVeraSafe ጋር በሚከተለው አድራሻ ግንኙነት ማድረግ ይቻላል:

VeraSafe፣ United Kingdom Ltd.
37 Albert Embankment
London SE1 7TL
United Kingdom

(c) የእርስዎ ፍቃደኝነት/ ፍቃድ

ይህ የግላዊነት መግለጫ የCupid Media'ን እርስዎ ድረገጹን እና የCupid Media ተያያዥ ድረገጾችን በሚጠቀሙበት ወቅት የእርስዎን የግል መረጃ/ ዳታ ከመሰብሰብ/ መቀበል እና መጠቀም ጋር ተያያዥነት ያላቸው ፖሊሲዎችን ይገልጻል። በትላልቅ ፊደላት የተጻፉት እንደ "የግል መረጃ/ ዳታ" እና "የግል መረጃ ልዩ ምድብ" የመሳሰሉት ቃላት በዚህ የግላዊነት መግለጫ አንቀጽ 1.8 ስር ፍቺ ተሰጥቷቸዋል።

እርስዎ ወደ ድረገጹ ሲገቡና ድረገጹን ሲጠቀሙ በዚህ የግላዊነት መግለጫ ድንጋጌዎች መሰረት በግል መረጃዎ መወሰድና ጥቅም ላይ መዋል ላይ ይስማማሉ። የግል መረጃዎን በማስመዝገብ ወይም በድረገጹ ወይም ተያያዥነት ባለው ድረገጽ ላይ በአባልነት በመመዝገብ በግል መረጃዎ እና ልዩ የግል መረጃ ምድብ መሰብሰብ እና ጥቅም ላይ መዋል ላይ ይስማማሉ።

የግል መረጃዎን እንድንሰበስብና እንድንጠቀም የሰጡንን ፍቃድ በየትኛውም ጊዜ ተገቢውን ድረገጽ ወይም ተያያዥ ድረገጽ መጠቀምዎን በማቋረጥ ሊሰርዙ ይችላሉ። እርስዎ የግል መረጃዎን የፈጠሩ አባል ከሆኑ የግል መረጃዎን እና ልዩ የግል መረጃ ምድብን እንድንሰበስብ እና እንድንጠቀም የሰጡንን ፍቃድ የግል መረጃዎን መጠቀምዎን በማቋረጥ እና የግል መረጃዎ እንዲታገድ ወይም እንዲሰረዝ ጥያቄ በማቅረብ ሊሰርዙ ይችላሉ። የእገዳ ወይም የመሰረዝ ጥያቄዎችዎን በግል መረጃዎ አማካኝነት ወይም በዚህ የግላዊነት መግለጫ አንቀጽ 1.1(ለ) ስር የተካተተውን የግንኙነት መረጃችንን ተጠቅመው ከእኛ ጋር ግንኙነት በማድረግ ማቅረብ ይችላሉ።

እባክዎ እኛ ከእርስዎ የወሰድነውን የትኛውንም የግል መረጃዎን ለመሰረዝ በዚህ የግላዊነት መግለጫ አንቀጽ 1.6(ረ) ስር የተገለጸውን የአሰራር ሂደት በመጠቀም ጥያቄዎን ማቅረብ ይኖርብዎታል።

1.2 ማንነትን አለመግለጽ

በ Cupid Media ሚዲያ በሚቀርቡት አገልግሎቶች ባህሪ የተነሳ ሙሉ ስምዎን በማናውቅበት ሁኔታ እርስዎን ለማስተናገድ አንቸገራለን። አገልግሎቶቻችንን ለመጠቀም በሚመዘገቡበት ወቅት ማንነትዎን በግልጽ እንዲያሳውቁ እና እውነተኛና ትክክለኛ መረጃዎን እንዲጠቀሙ ይጠየቃሉ።

1.3 የዳታ ስብሰባ

(ሀ) ለሁሉም ተጠቃሚዎች

ድረገጻችንን በሚጎበኙነት (አባል ያልሆኑ ተጠቃሚዎችን ጨምሮ) በየትኛውም ጊዜ ሰርቨሮቻችን ወዲያውኑ የእርስዎን የሚከተሉትን ጨምሮ የድረገጽ አጠቃቀም በተመለከተ ለስታቲስቲክስ አላማዎች መረጃ ይመዘግባሉ፡

(i) የሚጠቀሙበት የኢንተርኔት ማውጫ አይነት፣
(ii) የመራዎ URL፣
(iii) የIP አድራሻዎ፣
(iv) ያዩዋቸው ድረገጾች ብዛትና አይነት፣
(v) ድረገጾቹን የጎበኙባቸው ቀናትና ሰአቶች
(vi) የመውጫ URL.

ይህ ስለ እርስዎ በተመለከተ የምንሰበስበው መረጃ የግል መረጃ ካለመሆኑም በተጨማሪ በማናቸውም ሁኔታ ማንነትዎ አይታወቅም። ማንነትዎ ያልተገለጸበትን መረጃ እርስዎ በአባልነት ካልተመዘገቡ ወይም በሚጠቀሙበት ወቅት በአባልነት ካልተመዘገቡ በስተቀር ከየትኛውም ሌላ የግል መረጃ ጋር አናገናኝም። በዚህም መሰረት በድረገጹ ላይ ለምሳሌ፡ በአባልነት በመመዝገብ ወይም ወደ ድረገጹ በሚገቡበት ወቅት እንደ አባል በመመዝገብ ስለ ማንነትዎ ካልገለጹ የእርስዎን ድረገጻችንን የመጠቀም ምዝገባ/መረጃ በግል ከእርስዎ ጋር አናገናኘውም።

(ለ) ለአባላት

የእርስዎን በአባልነት መመዝገብ ተከትሎ ለእርስዎ ሙሉ የአባልነት ጥቅሞችን ለማቅረብ ያስችለን ዘንድ ስለ እርስዎ የተመለከቱ መረጃዎች እንሰበስባለን። ለመጀመሪያ ጊዜ በሚመዘገቡበት ወቅት እና ከዚያ በኋላ ከጊዜ ወደ ጊዜ ተጨማሪ መረጃ የሚያቀርቡልን ከሆነ ማንነትዎን ለይቶ የማያሳውቅ መረጃ እና የግል መረጃዎን በቀጥታ ከእርስዎ እንሰበስባለን።

በ Cupid Media ሊሰበሰብ የሚችል የግል መረጃ/ ዳታ የሚከተሉትን ያጠቃልላል:

(i) ሙሉ ስምዎን፣
(ii) የኢሜይል አድራሻዎን ፣
(iii) የመኖሪያ አድራሻዎን፣
(iv) ስልክ ቁጥርዎን፣
(v) የእርስዎን ፎቶግራፍ፣
(vi) እድሜዎን፣
(vii) ስራዎን፣
(viii) የአካል ገጽታዎን የተመለከተ ዝርዝር፣
(ix) ክሬዲት ካርድና የክፍያ መረጃዎን (እርስዎ የሚሰጡን ከሆነ)።

ለህግ ማስከበር እና እርስዎን አገልግሎቶቻችንን በአግባቡ እንዲጠቀሙ ለማስቻል አላማ በተጨማሪም የሚከተሉትን ጨምሮ የተወሰኑ ልዩ የግል መረጃ ምድብ መረጃዎችን ልንሰበስብ እንችላለን፡

(i) የዘር ግንድዎ ወይም የዘር ሀረግዎን፣
(ii) የፖለቲካ አመለካከቶችዎን፤
(iii) ሀይማኖትዎ ወይም ትስስርዎን፣
(iv) የፍልስፍና እምነቶችዎ ወይም የሰራተኛ ማህበር አባልነትዎን፣
(v) የጤና ሁኔታዎን፣
(vi) የጾታ ምርጫዎችዎ፣ አሰራሮችዎ ወይም ፍላጎቶችዎን
(vii) የወንጀል ሪከርድዎን (የዩኤስኤ ነዋሪ ከሆኑ)።

ወደ ድረገጹ በመግባትና በመጠቀም በዚህ የግላዊነት መግለጫ ድንጋጌዎች መሰረት በእርስዎ የልዩ የግል መረጃ ምድብ መረጃዎች መሰብሰብና ጥቅም ላይ መዋል ላይ በግልጽ ይስማማሉ።

(ሐ) የመረጃ መውሰጃ/Cookies እና ሌሎች የመረጃ መፈለጊያ ቴክኖሎጂዎች

በድረገጻችን ላይ ያልዎትን ተሞክሮ ለማሻሻል የመረጃ መውሰጃ እና እንደ ፒክስል ታጎች፣ የድረገጽ ማብሪያዎች፣ የመጠቀሚያ መሳሪያ አይዲዎች ወይም የማስታወቂያ አይዲዎች ያሉ ሌሎች የመረጃ መፈለጊያ ቴክኖሎጂዎችን ልንጠቀም እንችላለን።

የመረጃ መውሰጃዎች/ cookies መጠቀምን ከኢንተርኔት ማውጫዎ ላይ ተገቢ ሴቲንጎችን በመምረጥ ላይፈቅዱ ይችላሉ፤ ሆኖም እባክዎ ይህን የሚያደርጉ ከሆነ የድረገጻችንን የተሟሉ አገልግሎቶች መጠቀም ላይችሉ እንደሚችሉ ይገንዘቡ።

ድረገጻችን በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በድረገጽ የሚተላለፉ መረጃዎችን ወደ ጎግል ሰርቨሮች የሚያሰራጨው አገልግሎት ጉግል አናሊቲክስን ይጠቀማል። የጉግል አናሊቲክስ የግለሰብ ተጠቃሚዎችን ማንነት ለይቶ አያሳውቅም ወይም የእርስዎን የ IP አድራሻ ከየትኛውም ሌላ በጉግል ከተያዘ ዳታ ጋር አያገናኝም። ከጉግል አናሊቲክስ የምናገኛቸውን ሪፖርቶች የድረገጹን የመረጃ ዝውውርና አጠቃቀም ለመገንዘብ እንዲያግዘን እንጠቀምበታለን።

የጎግል አናሊቲክስን ማስታወቂያዎችን ለማየት ለጎግል አካውንትዎ የማስታወቂያ ሴቲንጎችን በመጠቀም ሊጭኑት ወይም ሊመርጡት ይችላሉ።

ድረገጻችን ከዚህ በታች በተመለከቱት ላይ ጎግል አናሊቲክስን ለመደገፍ የመረጃ መውሰጃና የተለያዩ የመረጃ መፈለጊያ ቴክኖሎጂዎችን ይጠቀማል:

(i) የጎግል ማርኬቲንግ ፕላትፎርም ጥምረቶች፣
(ii) ሥለ ሥነ ህዝብና ፍላጎት ሪፖርት ማድረግ፣
(iii) አገልግሎቶቻችንን በኢንተርኔት ለማስተዋወቅ በድጋሚ ለሽያጭ ማስተዋወቅን እና የጎግል ማሳያ ሳቢነትን ሪፖርት ማድረግን ጨምሮ ማስታወቂያ ለማሳየት፣
(iv) በእርስዎ የቀዳሚ ጊዜ የድረገጻችን ጉብኝቶች ላይ ተመስርተን የማስታወቂያ አገልግሎቶችን ለማሳደግና ግላዊ ለማድረግ፣ እና
(v) በማስታወቂያ ትኩረት መሳቢያዎች አማካኝነት የሚካሄዱ የማስታወቂያ አጠቃቀሞችና ግንኙነቶች እና እነዚህ ድረገጻችንን ከመጎብኘት ጋር እንዴት እንደሚገናኙ ሪፖርት ለማድረግ

የመረጃ መውሰጃዎችና ሌሎች የመረጃ መፈለጊያ አገልግሎቶች በተጨማሪም በሌሎች ሶስተኛ ወገኖች የሚካሄዱ ትንተናዎችን ለመደገፍ ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ።

(መ) የሶስተኛ ወገን ግንኙነቶች

በድረገጾቻችን ላይ ለሚተላለፉ ማስታወቂያዎች አገልግሎት ለመስጠት የተፈቀደላቸው አገልግሎት አቅራቢዎችን፣ የማስታወቂያ ኩባንያዎችን፣ የዳታ አስተዳደር ፕላትፎርሞችን እና የማስታወቂያ ኔትወርኮችን ጨምሮ ለሶስተኛ ወገኖች ፍቃድ ልንሰጥ እንችላለን።እንዲሁም፣ ለትንታኔ ዓላማዎች እና የማስታወቂያ ዘመቻዎችን በሚፈለገው መልኩ ለመዘጋጀት የፕሮፋይል ዳታዎን ከCupid Media ተባባሪ ኩባንያዎች ጋር ልንጋራ እንችላለን።

እነዚህ ኩባንያዎች ማስታወቂያዎቻቸውን ስለሚያዩ ወይም ግንኙነት ስለሚያደርጉ ተጠቃሚዎች የተመለከቱ መረጃዎችን ለመሰብሰብ የመረጃ መፈለጊያ ቴክኖሎጂዎችን ሊጠቀሙ ይችላሉ (ለምሳሌ፡ መረጃ መውሰጃዎች፣ የፒክስል ታጎች፣ የድረገጽ ማብሪያዎች፣ የመሳሪያ አይዲዎች ወይም የማስታወቂያ አይዲዎች)። እነዚህ ሶስተና ወገኖች በመረጃ መውሰጃዎች አማካኝነት የሚሰበስቧቸው የትኛውም መረጃዎች በምንም አይነት ሁኔታ ማንነትን አይገልጹም እንዲሁም ለይተው አያሳውቁም። የእነዚህ ሶስተና ወገኖች ምሳሌዎች የሚከተሉትን ያጠቃልላሉ: 360, Adobe, Akamai, Appnexus, Baidu, Bing, Cake, chargeback.com, Criteo, District M, Ecom Services, Facebook, Firebase, Google Ads, Google Ads Manager, Google Analytics, HotJar, Index Exchange, Naver, Olark, Oracle, Publift, Pubmatic, Pusher, RayGun, Rubicon Project, SDL, Sentient, Taboola, TikTok, Twitter, Urban Airship, Visa Inc, Yahoo, Yandex, Zendesk, Zero Bounce።

የኢንተርኔት ማውጫዎን ተገቢ ሴቲንጎች በመምረጥ ወይም በ አማካኝነት የግል መረጃዎን በመዝጋት የሶስተኛ ወገኖች ዳታ ስብሰባን መከልከል ይችላሉ። .

በድረገጻችን ላይ በተጨማሪም በዚህ የግላዊነት መግለጫ መሰረት የማይሰሩና ከእኛ ቁጥጥር ውጭ የሆኑ የሶስተኛ ወገኖች ድረገጾችን ማግኘት የሚችሉባቸው በርካታ የተለያዩ ቦታዎች አሉ። እነዚህ የሶስተኛ ወገን ድረገጾች የግል መረጃዎን ሊሰበስቡ ይችላሉ። የሁሉንም የሚጎበኟቸው የሶስተኛ ወገን ድረገጾችን የግላዊነት ፖሊሲ እንዲጠይቁ እንመክርዎታለን።

(ሠ) ማህበራዊ ሚዲያ

Cupid Media እንደ Facebook, Twitter, YouTube, Instagram, Pinterest, Weibo እና ሌሎችም ከመሳሰሉት የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ጋር በቅንጅት ይሰራል። በእነዚህ አገልግሎቶች አማካኝነት በድረገጻችን ላይ መረጃን "like" ወይም "share" ያድርጉ የሚለውን ከመረጡ የተገቢ አገልግሎቶችን የግላዊነት ፖሊሲ ማየት አለብዎ። የማህበራዊ ሚዲያ ድረገጽ አባል ከሆኑ ቅንጅቶቹ የማህበራዊ ሚዲያ ገጹን የእርስዎን የዚህ ድረገጽ መጎብኘት ከሌሎች የግል መረጃዎች ጋር እንዲያገናኝ ያስችሉታል።

1.4 የግል መረጃን የመሰብሰብ፣ የመያዝ፣ የመጠቀምና የመግለጽ አላማዎች

(ሀ) ከእርስዎ ብቻ መሰብሰብ

ማድረጉ አሳማኝነት ያለውና የተለመደ አሰራር ሆኖ ከተገኘ ስለ እርስዎ የተመለከቱ የግል መረጃዎችዎን በቀጥታ ከእርስዎ ልንሰበስብ እንችላለን።

(ለ) የግል መረጃ የመሰብሰብ አላማዎች

ለሚከተሉት አላማዎች አሳማኝነት ባለው መልኩ አስፈላጊ የሆኑ የግል መረጃዎችን ብቻ እንሰበስባለን፡

(i) የአባልነት ማመልከቻዎን ተቀብለን ለማስተናገድ እና ለእርስዎ አገልግሎቶች ማቅረብ የሚያስችሉን (በይፋ የሚታይ የግል መረጃ መፍጠርን፣ አባላትን የሚስማሙዋቸው አበባላትን እንዲፈልጉ ማስቻልን እና በአባላት መካከል የሚካሄድ ግንኙነት የአሰራር ዘዴዎች ማቅረብን ጨምሮ)፣
(ii) ለውስጥ ምርምርና የስታቲስቲክስ አላማዎቻችን (የገበያ ምደባና የደንበኞች አስፈላጊነት ትንተናን ጨምሮ)፣
(iii) ለእርስዎ ይፈልጓቸዋል ብለን ያመንንባቸው ሌሎች መረጃዎችና የመረጃ ግብአቶችን ለእርስዎ መላክ የሚያስችሉን፣
(iv) እርስዎ የሚከፍሉንን ክፍያዎች ተቀብለን ለማስተናገድ የክፍያ ማስተናገጃ ማግኘት የሚያስችሉን፣ እና
(v) ለየትኛውም ሌሎች በድረገጻችን ላይ ማግኘት በሚችሏቸው የአጠቃቀም ድንጋጌዎች ስር ለተገለጹ ልዩ አላማዎች የሚያገለግሉን

(የ"መጀመሪያ ደረጃ አላማ")።

ለየትኛውም የንግድ ስራ አላማዎች (የንግድ ስራ አላማው በልዩ ሁኔታ በዚህ የግላዊነት መግለጫ ስር ካልተገለጸ በስተቀር) የግል መረጃዎችን ለየትኛውም ሶስተኛ ወገኖች አንሸጥም ወይም አንሰጥም።

(ሐ) የግል መረጃን መጠቀምና መግለጽ/ ይፋ ማድረግ

ለመጀመሪያ ደረጃ አላማዎች የግል መረጃን መጠቀም የግል መረጃን ለአውቶማቲክ የውሳኔ አሰጣጥ ሂደተች መጠቀምን ያጠቃልላል።

ስለ እርስዎ የተመለከተ የግል መረጃዎን የምንጠቀመው ወይም የምንገልጸው ከመጀመሪያ ደረጃ አላማ ውጭ ለሆኑ አላማዎች (ለ "ሁለተኛ ደረጃ አላማዎች") ብቻ ሆኖ የሚከተሉት ተፈጻሚ ሲሆኑ ብቻ ነው:

(i) የሁለተኛ ደረጃ አላማው ከመጀመሪያ ደረጃ አላማ ጋር ግንኙነት ካለው እና የግል መረጃው የልዩ የግል መረጃ ምድብ መረጃ ከሆነ፣ ሁለተኛ ደረጃ አላማው በቀጥታ ከመጀመሪያ ደረጃ አላማ ጋር የሚገናኝ ከሆነ፣ እና
(ii) የግል መረጃዎን ለሁለተኛ ደረጃ አላማ አሳማኝነት ባለው መልኩ እንደምንጠቀም ወይም እንደምንገልጽ የሚብቁ ከሆነ፣ ወይም
(iii) የግል መረጃዎን ለሁለተኛ ደረጃ አላማ እንድንጠቀም ወይም እንድንገልጽ ከፈቀዱልን፣ ወይም
(iv) የግል መረጃን መጠቀም ወይም መግለጽ በህግ፣ ደንብ ወይም የፍርድ ቤት ትእዛዝ የሚጠየቅ ወይም የሚፈቀድ ከሆነ።

ምርቶቻችንና አገልግሎቶቻችንን ለእርስዎ ለማስተዋወቅ በተጨማሪም እንደ ፌስቡክ ላሉ ሶስተኛ ወገኖች እንደ የፌስቡክ መደበኛ ተከታዮች ያሉ ውጤቶችን በመጠቀም አማካኝነት ማስታወቂያዎቻችንን የበለጠ እርስዎ ላይ ኢላማ እንዲያደርጉ ለማስቻል የኢሜይል አድራሻዎን በከፊል (ሆኖም ምንም ሌላ የግል መረጃ አይጨምርም) ልንሰጥ እንችላለን።

የእርስዎ ከፊል የኢሜይል አድራሻ ንጽጽር የሚካሄደው እቃዎቻችንና አገልግሎቶቻችንን ለእርስዎ ለማስተዋወቅ አላማ ብቻ ሲሆን ለየትኛውም አላማ በሶስተኛ ወገን ጥቅም ላይ አይውልም። የከፊል የኢሜይል አድራሻዎ ንጽጽር የእርስዎን ማንነት ወይም የኢሜይል አድራሻዎን በሚያሳውቅ መልኩ ጥቅም ላይ የማይውሉ ከመሆኑም በተጨማሪ እርስዎን የተመለከተ ምንም ሌላ ተጨማሪ መረጃ በእኛ ለሶስተኛ ወገን አይሰጥም።

የግል መረጃዎን ለመጀመሪያ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ አላማዎች እንድንጠቀም የሰጡንን ፍቃድ በየትኛውም ጊዜ በዚህ የግላዊነት መግለጫ አንቀጽ 1.1(ለ) ስር የተገለጸውን የግንኙነት አድራሻችንን ተጠቅመው ከእኛ ጋር ግንኙነት በማድረግ ሊሰርዙ ይችላሉ። ሆኖም ይህ ድረገጹን እና የCupid Media አገልግሎቶችን በማግኘት ችሎታዎ ላይ ተጽእኖ ሊፈጥር ወይም አጠቃቀምዎን ሊገድብ ይችላል።

(መ) የግል መረጃ መያዝ

በእኛ የተያዘ የግል መረጃዎን ከታች ከተመለከቱት ለመጠበቅ ተመራጭ የአሰራር ሂደቶችን እጠቀማለን እንዲሁም ሁሉንም አሳማኝ እርምጃዎች እንወስዳለን:

(i) ያልተገባ አጠቃቀም፣ ጣልቃ መግባት እና መጥፋት፣ እና
(ii) ያልተፈቀደ ማግኘት፣ ማሻሻል ወይም መግለጽ

ባልተለመዱ ሁኔታዎች መብቶችዎንና ነጻነትዎን አደጋ ላይ የሚጥል ከባድ የዳታ ጥሰጥ የሚፈጸም ከሆነ ይህን ምንም ሳንዘገይ በአስቸኳይ በሀገርዎ ለሚገኝ የሚመለከተው ተቆጣጣሪ ባለስልጣን እናሳውቃለን። በተጨማሪም ከባድ የዳታ ጥሰት በመብቶችዎና ነጻነትዎ ላይ ተጽእኖ የሚፈጥርበት ሁኔታ ሲያጋጥም ስለ ጥሰቱ ለእርስዎ እናሳውቅዎታለን።

(ሠ) የውጭ ሀገር ገለጻዎች

የትኛውም ለእኛ የሚሰጡን የግል መረጃዎ ላይ የሚገባ መረጃ ተመልካቹ የሚገኝበት ቦታ የትም ይሁን የት በግል መረጃዎ ላይ በይፋ ይታያል። የግል መረጃዎን በሚፈጥሩበት ወቅት የውጭ ሀገር ተቀባዮች የግል መረጃዎን ማየት የሚችሉ መሆኑን በተመለከተ ማረጋገጫ ይሰጣሉ።

የደንበኛ ድጋፍ መስጠት፣ የጀርባ የቢሮ ተግባሮችን ማከናወን፣ ማጭበርበርን የመከላከል ተግባሮችን ማከናወን ወይም ለእርስዎ አገልግሎቶች ለማቅረብ ያስችለን ዘንድ ለሰራተኞቻችን ወይም አቅራቢዎቻችን (እነርሱም ሆኑ አገልግሎት መስጫዎቻቸው ከእርስዎ የመኖሪያ ሀገር ውጭ ሊሆኑ ለሚችሉ) የሰጡንን የግል መረጃ፣ የክፍያ መረጃ ወይም ሌሎች የግል መረጃዎችዎን እንዲያዩ ልንፈቅድ እንችላለን።

የግል መረጃዎን ደህንነት ለመጠበቅ የደህንነት እርምጃዎችን ተግባራዊ አድርገናል። ሆኖም እንደ የየትኛውንም ዳታ መተላለፍ ሁሉ አሁንም በዳታ ላይ የሚፈጸሙ ጥሰቶች ስጋቶች አሉ። የግል መረጃዎ የአጠቃላይ የዳታ ጥበቃ ደነብ ኮሚሽን የውሳኔ ብቁነት ወይም በሀገርዎ የሚገኝ አቻ ተቆጣጣሪ ባለስልጣን ህጎች ለማይመለከታቸው ሶስተኛ አገራትና አለም አቀፍ ድርጅቶች የሚተላለፍባቸው ሁኔታዎች አሉ። ይህ የመረጃ ማስተላለፍ ለእኛ በCupid Media ድረገጽ የአጠቃቀም ህጎች ስር የጠገለጹትን ግዴታዎቻችንን ለመፈጸም እና ለእርስዎ አገልግሎቶቻችንን ለማቅረብ አስፈላጊ ነው።

የግል መረጃዎን እና የልዩ የግል መረጃ ምድብ መረጃዎን በማቅረብ በዚህ የግላዊነት መግለጫ መሰረት ለዚህ መረጃ አለም አቀፍ ማስተላለፍና ማስተናገድ ከማስተላለፉና ማስተናገዱ ጋር ተያያዥነት ስላላቸው ስጋቶች በተሟላና በመረጃ ላይ የተመሰረተ እውቀት ላይ ተመስርተው በግልጽ ፍቃድዎን ይሰጣሉ።

ፍቃድዎን በዚህ የግላዊነት መግለጫ አንቀጽ 1.1(ለ) ስር የተገለጸውን የግንኙነት አድራሻችንን ተጠቅመው ከእኛ ጋር ግንኙነት በማድረግ በየትኛውም ጊዜ መሰረዝ ይችላሉ። ሆኖም ይህ ድረገጹን እና የCupid Media አገልግሎቶችን በማግኘት ችሎታዎ ላይ ተጽእኖ ሊፈጥር ወይም አጠቃቀምዎን ሊገድብ ይችላል።

በሁሉም ሌሎች ሁኔታዎች የግል መረጃዎን ለሶስተኛ ወገን ሀገር ተቀባይ ወይም አለም አቀፍ ድርጅት የምንገልጸው መረጃውን መግለጽ በህግ፣ ደንብ ወይም የፍርድ ቤት ትእዛዝ የሚጠየቅ ወይም የሚፈቀድ ከሆነ ብቻ ነው።

(ረ) ባለማስገደድ የተገኘ መረጃ

እርስዎን በተመለከተ እኛ ያልፈለግነው ወይም ያልጠየቅነውን የግል መረጃ የምንቀበል ከሆነ እና መረጃውን ለመሰብሰብ በህግ እንደሚፈቀድልን ከወሰንን መረጃውን በዚህ የግላዊነት መግለጫ መሰረት እንጠቀምበታለን። በሁሉም ሌሎች ሁኔታዎች ህጋዊና አሳማኝነት ያለው ሆኖ በሚገኘው መሰረት ተገቢ የግል መረጃን እንሰርዛለን ወይም እንዳይታወቅ እናደርጋለን።

(ሰ) ሚስጥር ያልሆነ መረጃ

በየትኛውም ሌላ አባል የግል መረጃ ስር እንዲካተት የሚሰጡን ሰነድ ወይም መረጃ የሚስጥር ያልሆነና የባለቤትነት መብት የማይነሳበት ተደርጎ ይቆጠራል። ይህን ሰነድ ወይም መረጃ ያለ ምንም ገደብ እንጠቐምበታለን። በተለይም Cupid Media እርስዎ የሰጡንን ይህን ሰነድ ወይም መረጃ (የትኛውንም የግል መረጃ፣ ቪዲዮ ወይም የድምጽ ቅጂዎችን ጨምሮ) የግል መረጃዎን በየትኛውም ሌላ ተገቢ ባለቤትነቱ የCupid Media በሆነና በ Cupid Media ስር ሚሰራ የማቀጣጠሪያ ድረገጽ ላይ ኮፒ ለማድረግ ይጠቀምበታል። የትኛውም ይህ በእርስዎ የተሰጠ ሰነድ ወይም መረጃ የድረገጹ ሌሎች አባላት ወይም ተጠቃሚዎች እንዲያነቡት ይሰጣል።

(ሸ) ግንኙነት

የተመከሩ የግል መረጃዎዎች ማገናኘትንእንደ የፍላጎት መግለጫ ማሳወቂያዎች ወይም የመልአክት ማሳወቂዎች ተግባሮች ማስታወቂያዎች፣ ማስታወቂያዎች ወይም ሽያጮች፣ በአገልግሎቶቻችን ላይ የሚደረጉ ለውጦች ወይም ጭማሪዎች፣ ወይም የንግድ ስራ ተባባሪዎቻችን የትኛውንም ምርቶችና አገልግሎቶችን በተመለከተ ለእርስዎ የኤሌክትሮኒክስ መልእክት የመላክ መብታችን የተጠበቀ ነው።

የድረገጻችን አባል ከሆኑ የትኞቹን አይነት የኢሜይል ግንኙነቶች መቀበል እንደሚፈልጉ ለማሳወቅ በ"Notifications" ገጽ ላይ የሚገኙ ሴቲንጎችን በመጠቀም የኢሜይል ምርጫዎችዎን መቆጣጠር ይችላሉ።

1.5 የግል መረጃን ማስወገድ

የግል መረጃዎን የምንይዘው ለህጋዊ የስራ አላማዎች ለምንፈልገው እና በተፈጻሚ ህግ ለሚጠየቀው ጊዜ ብቻ ነውበሚከተሉት ሁኔታዎች ስለ እርስዎ በተመለከተ የያዝነውን የትኛውንም የግል መረጃዎን ለመሰረዝ አሳማኝ እርምጃዎችን እንወስዳለን:

(i) የግል መረጃውን ወደፊት ለተሰበሰቡበት አላማዎች የማንፈልገው ከሆነ እና መረጃውን ይዘን የመቆየት ፍቃድ ከሌለን፣ እና
(ii) መረጃውን ለመያዝ በህግ፣ ደንብ ወይም በፍርድ ቤት ትእዛዝ የማንጠየቅ ወይም የማንገደድ ከሆነ።

በዚህ የግላዊነት መግለጫ መሰረት የተወሰኑ መረጃዎች ለሶስተኛ ወገኖች ተሰጥተው ከሆነ መረጃዎቹን መያዝ በሚመለከተው ሶስተኛ ወገን ፖሊሲዎች ላይ የተመሰረተ ነው።

1.6 ማግኘት፣ ማስተካከልና መያዝ

(ሀ) የግል መረጃን ማግኘት

ከእርስዎ ጋር በተያያዘ በእኛ የተያዘ የግል መረጃን ከጠየቁን ከሚከተሉት ሁኔታዎች በስተቀር እንሰጥዎታለን:

(i) መረጃውን መስጠት ህገወጥ ካልሆነ፣ ወይም
(ii) መረጃውን አለመስጠት በተገቢ ሀህግ፣ ደንብ ወይም የፍርድ ቤት ትእዛዝ ካልተጠየቀ ወይም ከተፈቀደ

የግል መረጃዎን እንድንሰጥዎ ለመጠየቅ እባክዎ በዚህ የግላዊነት መግለጫ አንቀጽ 1.1(ለ) ስር የተገለጸውን የግንኙነት አድራሻችንን በመጠቀም ከእኛ ጋር ግንኙነት ያድርጉ።

ጥያቄዎን ያቀረቡልን መሆኑን ተከትሎ ጥያቄዎ ከሚደርሰን ቀን ጀምሮ በአንድ (1) ወር ጊዜ ውስጥ ከእርስዎ ጋር ግንኙነት በማድረግ በአንዳንድ ምክንያቶች የግል መረጃውን ለመያዝ ካልወሰንን ወይም መረጃውን እንድንከለክል የሚጠይቅ ግዴታ ከሌለብን በስተቀር የጠየቁንን የግል መረጃ እንሰጥዎታለን።

(ለ) ለሶስተኛ ወገን መግለጽ

የግል መረጃዎን ለየትኛውም ሶስተኛ ወገኖች አንሸጥም። በዚህ የግላዊነት መግለጫ ስር በሌላ መልኩ ካልተገለጸ በስተቀር የግል መረጃዎን በተጨማሪም ለሌሎች የስራ አላማዎች ለየትኛውም ሶስተኛ ወገኖች አንገልጽም። ሆኖም ይህን በማይገድብ መልኩ በየትኛውም ጊዜ የግል መረጃዎን ለሶስተኛ ወገን አለመሸጡን የተመለከተ ማረጋገጫ እንድንሰጥዎ ሊጠይቁን፣ ወይም መረጃው ለንግድ ስራ አላማዎች የተሸጡለት ወይም የተገለጹለት ሶስተኛ ወገንን የትኛውንም ዝርዝር መረጃዎች እንድንሰጠጥዎ ሊጠይቁን ይቸላሉ።

(ሐ) የመረጃ መያዝ/ አያያዝ

የሌሎች ሰዎች መብቶችና ነጻነቶች ላይ ተጽእኖ እስካልፈጠረና እርስዎ ጥያቄዎን እስከገለጹልን ድረስ፡

(i) አውቶማቲክ የግል መረጃዎን ተቀብሎ ማስተናገጃ ተግባራዊ ካደረግን የዚህን የግል መረጃ ኮፒ በተደራጀ፣ በመደበኛነት የሚያገለግልና በማሽን ሊነበብ በሚችል ፎርማት እንሰጥዎታለን፣ እንዲሁም
(ii) ጥያቄዎ ከደረሰን በኋላ ከቴክኒክ አንጻር አዋጭ ሆኖ ከተገኘ የግል መረጃዎን በቀጥታ ለሌላ ዳታ ያዥ እናስተላልፋለን።

(መ) የንግድ ጥንቃቄ የሚፈልግ መረጃ

የግል መረጃዎን እንዲያገኙ ማድረግ የንግድ ጥንቃቄን የሚፈልግ መረጃን የሚያሳውቅ ከሆነ ይህን መረጃ ልንሰጥዎ አንችልም። ሆኖም ከውሳኔው በስተጀርባ ያለውን ምክንያት እናሳውቅዎታለን።

(ሠ) አገናኞችን መጠቀም

የግል መረጃዎን በቀጥታ ልናቀርብልዎ የማንችል ከሆነ አዋጭነት ያለው ሆኖ ከተገኘ ይህን የሚያቀርብልዎ የአገናኝ አገልግሎቶችን ልንቀጥር እንችላለን።

(ረ) የግል መረጃን ማስተካከልና መሰረዝ

ለእኛ የሰጡን የግል መረጃዎ እንደ አስፈላጊነቱ ትክክለኛና ወቅታዊ የግል መረጃዎ መሆኑን ማረጋገጥ የእርስዎ ኃላፊነት ነው። በየትኛውም ምክንያት በየትኛውም በእያ የተያዘ የግል መረጃዎ ላይ ማስተካከያ ማድረግ የማይችሉ ከሆነ እባክዎ በአንቀጽ 1.1(ለ) ስር የተገለጸውን የግንኙነት አድራሻ በመጠቀም ከእኛ ጋር ግንኙነት ያድርጉ።

ጥያቄዎ ከደረሰን በኋላ የግል መረጃዎ ላይ ማስተካከያ ማድረግን የማንመርጥ ከሆነ ፍቃደኛ ያልሆንንበትን ምክንያት እና አለመፍቀዳችንን ለመቃወም የሚያገኟቸው የአሰራር ዘዴዎችን በአንድ (1) ወር ጊዜ ውስጥ እናሳውቅዎታለን።

የግል መረጃዎ እንዲሰረዝልዎት የሚፈልጉ ከሆነ እባክዎ በአንቀጽ 1.1(ለ) ስር የተገለጸውን የግንኙነት አድራሻ በመጠቀም ከእኛ ጋር ግንኙነት ያድርጉ። የግል መረጃዎን ለመሰረዝ አሳማኝ እርምጃዎችን የማንወስድባቸው ሁኔታዎች መረጃውን በዚህ የግላዊነት ፖሊሲ ሌላ ድንጋጌ፣ GDPR ወይም የትኛውም ሌላ የህግ ምክንያት መያዝ የሚኖርብን ከሆነ ብቻ ናቸው። ሆኖም የግል መረጃዎን መሰረዝ የ Cupid Media የግል መረጃዎ እንዲሰረዝ ማለትም አገልግሎቶቻችንን ማግኘት እንዳይችሉ ሊያደርግ ይችላል።

ቀደም ሲል በዚህ የግላዊነት መግለጫ መሰረት ለሶስተኛ ወገን የገለጽነው የግል መረጃዎ ላይ ማስተካከያ የምናደርግ ወይም የምንሰርዝ ከሆነ ለሶስተኛ ወገኑ የመረጃውን መስተካከል ወይም መሰረዝ ለማሳወቅ እና ሶስተኛ ወገኑም ተመሳሳዩን እንዲያደርግ ለመጠየቅ አሳማኝ እርምጃዎችን እንወስዳለን።

(ሰ) ማስተካከያ ለማድረግ ወይም ለመሰረዝ ፍቃደኛ አለመሆን

በየትኛውም ጊዜ የግል መረጃዎን ለመስጠት ፍቃደኛ የማንሆን ወይም የምንከለክል ከሆነ ወይም የግል መረጃዎ ላይ ማስተካከያ ለማድረግ ወይም ለመሰረዝ ፍቃደኛ ካልሆንን ፍቃደኛ ያለመሆናችን ወይም የመከልከላችንን ምክንያት እናሳውቅዎታለን።

(ሸ) መረጃን የማስተናገድ ገደብ

የግል መረጃዎን የምንይዝበትና የምናትስተናግድበት አኳኋን ላይ ገደብ ወይም ክልከላ እንድናስቀምጥ ሊጠይቁን የሚችሉ ሲሆን በዚህ ጊዜ የግል መረጃዎን ተቀብለን የምናስተናግደው፡ በእኛ ላይ ለሚነሱብን የህግ ተጠያቂነቶች ለመዘጋጀት፣ ለመመለስና የመከላከያ መልስ ለማቅረብ፣ ወይም የሌላን ሰው መብቶች ለመጠበቅ እርስዎ በሚሰጡን ፍቃድ መሰረት ነው።

(i) ወጪዎች

ከግል መረጃዎ ጋር ተያያዥነት ያላቸው የትኛውንም ግንኙነቶች ጨምሮ የግል መረጃዎን ማቅረብ፣ መሰረዝና ማስተካከልአገልግሎትን በጠቅላላ በነጻ እናቀርብልዎታለን።

ጥያቄዎችዎ በአሳማኝነት በማስረጃ ላይ የተመሰረቱ ካልሆኑ ወይም በባህሪያቸው ከልክ ያለፉ ከሆኑ (በተለይም በተደጋጋሚነት በመቅረብ የተነሳ) መረጃውን ወይም ግንኙነቱን ለመስጠት፣ ወይም የጠየቁትን እርምጃ ለመውሰድ የተወሰነ አሳማኝነት ያለው ክፍያ ልናስከፍልዎ እንችላለን። ጥያቄዎችዎ በአሳማኝነት በማስረጃ ላይ የተመሰረቱ ካልሆኑ ወይም በባህሪያቸው ከልክ ያለፉ ከሆኑ በተጨማሪም ጥያቄዎን ላንቀበልዎ እንችላለን።

(j) ልዩ የመቃወም/ ያለመቀበል መብቶች

ከዚህ በታች በተመለከቱት ምክንያቶች ለእኛ የግል መረጃዎን ያለ እርስዎ ፍቃድ ተቀብለን ማስተናገድ አስፈላጊ ከሆነ:

(i) የማህበረሰቡን ጥቅም የሚያስጠብቅ ተግባር ለማከናወን፣
(ii) በይፋ የተሰጠንን ህጋዊ ስልጣን ለመጠቀም፣ ወይም
(iii) ይህን ማድረግ የእኛን ህጋዊ ጥቅሞች ወይም የሶስተና ወገን ህጋዊ ጥቅሞች የሚስጠብቅ ከሆነ፤

ይህን አይነቱን አጠቃቀም የመቃወም መብት አልዎት።

የግል መረጃዎን መጠቀማችንን የሚቃወሙ ከሆነ የግል መረጃዎን ለመጠቀም፣ ወይም ለሚነሱብን የህግ ጥያቄዎች ለመዘጋጀት፣ ለመከላከልና የመከላከያ መልስ ለማቅረብ አስገዳጅ ህጋዊ ምክንያቶች ካልኖሩ በስተቀር የግል መረጃዎን ከመጠቀም እንታቀባለን።

የግል መረጃዎን በዚህ የግላዊነት መግለጫ መሰረት ከሰበሰብን እና ይህን የግል መረጃ ከማርኬቲንግ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ላላቸው አላማዎች (እርስዎ ፍቃድ የሰጡባቸው) መጠቀምን የምንመርጥ ከሆነ ይህን አጠቃቀም በየትኛውም ጊዜ የመቃወም መብት አልዎት።

ተቃውሞዎን ከተቀበልን በኋላ በታቸለ መጠን ወዲያውኑ የግል መረጃዎን ከማርኬቲንግ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ላላቸው አላማዎች መጠቀማችንን እናቆማለን።

1.7 ቅሬታዎች

(ሀ) የቅሬታዎች አቀራረብ

የግል መረጃዎን ይህን የግላዊነት መግለጫ በሚጥስ አኳኋን ወይም ተፈጻሚ ህግን በሚጥስ መልኩ ተጠቅመናል ብለው ካመኑ ይህን በprivacy@cupidmedia.com.

ኢሜይል ሊያደርጉልን ይችላሉ።

ነዋሪነትዎ በአውሮፓ ህብረት ውስጥ ከሆነና የግል መረጃዎን በተመለከተ ቅሬታ ወይም ጥያቄ ካሉዎ በተጨማሪም የአውሮፓ ተወካያችን ከሆነው VeraSafe, ጋር በዚህ የግላዊነት መግለጫ አንቀጽ 1.1(ለ) ስር የተገለጸውን የግንኙነት መረጃ ተጠቅመው ግንኙነት ማድረግ ይችላሉ።

በተጨማሪም በሀገርዎ ለሚገኘው የሚመለከተው ተቆጣጣሪ ባለስልጣን የቅሬታ ማመልከቻ የማቅረብ መብት አልዎ። በሀገርዎ የሚገኘው የሚመለከተው ተቆጣጣሪ ባለስልጣን የትኛው እንደሆነ እርግጠኛ ካልሆኑ እባክዎ እገዛ እናደርግልዎ ዘንድ ከእኛ ጋር ግንኙነት ያድርጉ።

(ለ) የእኛ ምላሽ

ቅሬታዎ በደረሰን በ30 ቀናት ውስጥ ከቅሬታዎ ጋር በተያያዘ ምን እርምጃ ለመውሰድ እንዳቀድን በጽሁፍ እናሳውቅዎታለን እንዲሁም በምንሰጥዎ ምላሽ ካልረኩ ምን ተጨማሪ እርምጃዎችን መውሰድ እንደሚችሉ በተመለከተ ዝርዝር መረጃዎችን እንሰጥዎታለን።

1.8 ፍቺዎች

"ጠቅላላ የዳታ ጥበቃ ደንብ" እና "GDPR" ማለት የአውሮፓ ህብረት ፓርላማና ካውንስሉ በ27 ሚያዚያ 2016 ዓ.ም የግል መረጃዎችን ተቀብሎ በማስተናገድ እና የዚህ ዳታ በነጻ መዘዋወርን በተመለከተ ለተፈጥሮ ሰዎች ጥበቃ ለማድረግ የአውሮፓ ህብረት ፓርላማና ካውንስሉ ያጸደቁት እና መመሪያ ቁ. 95/46/ECን የሻረው ደንብ (EU) 2016/679 ነው።

"አለም አቀፍ ድርጅት" ማለት በማህበረሰብ አለም አቀፍ ህግ የሚተዳደር ድርጅትና ተባባሪ ድርጅቶቹ፣ ወይም የትኛውም ሌላ በሁለት ወይም ከዚያ በላይ ሀገራት መካከል በሚደረግ ስምምነት ላይ ተመስርቶ የሚቋቋም አካል ነው።

"የግል መረጃ" የትኛውም በግልጽ የሚታወቅ የተፈጥሮ ሰውን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በተለይም እንደ ስም፣ የመታወቂያ ቁጥር፣ የዳታ መገኛ ቦታ፣ የኦንላይን መታወቂያ ባሉ መለያዎች ወይም ከዚህ የተፈጥሮ ሰው ጋር ተያያዥ የሆኑ አንድ ወይም ከዚያ በላይ አካላዊ፣ የስነ ልቡና፣ የዘር፣ የአእምሮ፣ የኢኮኖሚ፣ የባህል ወይም የማህበራዊ ማንነት ምክንያቶች አማካኝነት ተለይቶ እንዲታወቅ የሚያደርግና የልዩ የግል መረጃ ምድብን የሚይዝ መረጃ ነው።

"ተቀብሎ ማሰናዳት" ማለት በአውቶማቲክ ዘዴዎች ይሁንም አይሁንም በግል መረጃ ወይም የተለያዩ የግል መረጃዎች ላይ የሚካሄዱ እንደ ስብሰባ፣ ምዝገባ፣ ማደራጀት፣ ማዋቀር፣ ማስቀመጥ፣ ለውጥ ማድረግ፣ አውጥቶ መጠቀም፣ ማማከር፣ መጠቀም፣ በማሰራጨት መግለጽ፣ ማሰራጨት ወይም በሌላ መልኩ መስጠት የመሳሰሉ የትኛውም አሰራር ወይም ተከታታይ አሰራሮች ናቸው።

"ልዩ የግል መረጃ ምድብ" ማለት የአንድን የተፈጥሮ ሰው ልዩ ሁኔታ ለይቶ ለማወቅ አላማ የሚጠቅም ዘር ወይም የዘር ሀረግ፣ የፖለቲካ አመለካከቶች፣ ሀይማኖት ወይም የእምነት ፍልስፍናዎች፣ የሰራተና ማህበር አባልነት፣ የወንጀል መዝገብ፣ የዘረመል ወይም የአሻራ መረጃን፣ የጤና መረጃን ወይም የእርስዎን ጾታ ወይም የጾታ ምርጫን የተመለከተ መረጃን የሚገልጽ የግል መረጃ ነው።

"ተያያዥ ድረገጽ" ማለት በCupid Media Pty Ltd ACN 104 844 564 ባለቤትነት፣ አንቀሳቃሽነት ስር የሚሰራ ወይም ቁጥጥር የሚደረግበት የትኛውም ሌላ ድረገጽ ነው።