የፍቅር ጓደኝነት ደህንነት

የኦንላይን ደህንነት

የግል መረጃ /ፕሮፋይል/ መፍጠር

ብዙዎቻችን እንዴት ማራኪ የኦንላይን የመቀጣጠሪያ የግል መረጃ እንደምንፈጥር ቢያውቁም እንኳ አንዳንዶች ከልክ በላይ አልፈው ይሄዱና ከአስፈላጊው በላይ መረጃ ይገልጻሉ።

የኦንላይን የመቀጣጠሪያ የግል መረጃ ማራኪና ጋባዥ መሆን አለበት፤ ሆኖም ይህ ለአጭበርባሪዎች የእርስዎን ዝርዝር መረጃ በቀላሉ የሚያገኙበት መንገድ የሚፈጥር መሆን የለበትም። የኦንላይን የመቀጣጠሪያ የግል መረጃ በሚፈጥሩበት ወቅት በአእምሮዎ ውስጥ ስለ ደህንነትዎም አብረው ያስቡ።

በአእምሮዎ ውስጥ መርሳት የሌለብዎ ነገሮች:
  • ተገቢ የተጠቃሚ ስም ይጠቀሙ
  • ለመገመት አስቸጋሪ የሆነ የይለፍ ቃል ይጠቀሙ
  • ግላዊ መረጃዎችን በሚስጥር ይያዙ
ደህንነቱ የተጠበቀ መጨዋወት፣ ደህንነታቸው የተጠበቀ የስልክ ጥሪዎች እና የሥነ ልቡና ደህንነት
ወደ ነገሮች በችኮላ አይግቡ። በCupid ፕላትፎርም ላይ ከሚያውቁት ሰው ጋር ውይይት ማድረግዎን እንዲቀጥሉ እንመክርዎታለን። መጥፎ ሀሳቦች ያሏቸው ተጠቃሚዎች በአብዛኛው ውይይቱን ወዲያውኑ ወደ ውይይት ጽሁፍ፣ የጽሁፍ መልእክት መተግበሪያዎች፣ ኢሜይል ወይም ወደ ስልክ ሊያስተላልፉት ይሞክራሉ።
በረጅም ርቀት ወይም የውጭ አገር ግንኙነቶች ላይ ጥንቃቄ ያድርጉ
ከእርስዎ አገር እንደሆኑ የሚነግሩዎ ሆኖም ውይይቱን ‘ወዳልተፈለገ አቅጣጫ’ የሚወስዱ ለምሳሌ፡ ወደ አገራቸው ለመመለስ የሚረዳቸው ገንዘብ የሚጠይቁዎትን አጭበርባሪዎች ይጠንቀቁ። አጭበርባሪዎች በአብዛኛው በአካል መገናኘትን ወይም በስልክ/በቪዲዮ ጥሪ ማውራትን አይፈልጉም - ይህ ምናልባትም እነርሱ የነገሩዎትን አይነት ሰዎች ስላልሆኑ ይችላል። አንድ ሰው ጥያቄዎችዎን ሆን ብሎ ካልመለሰልዎ ወይም በቅድሚያ ሳያገኝዎት ወይም ሳያውቀዎት ጥብቅ ግንኙነት እንድትመሰርቱ የሚገፋፋዎ ከሆነ — ይህ የመጀመሪያው የጥንቃቄ ምልክት ነው።
የግል መረጃዎን ይጠብቁ
ለማያውቋቸው ሰዎች በፍጹም - እንደ መኖሪያዎ ወይም የስራ አድራሻዎ የመሳሰሉ የግል መረጃዎችዎን ፣ ወይም ስለ እለታዊ መደበኛ ተግባሮችዎ (ለምሳሌ፡ በየዕለቱ ጠዋት ወደታወቀ ካፌ የሚሄዱ ስለመሆኑ) አያጋሩ። ልጆች ካሉዎ ልጆችዎን በተመለከተ በኦንላይን ለሚያውቁት ሰው የሚያጋሩትን መረጃ መገደብ ተመራጭ ነው። የልጆችዎን ስሞች ወይም ትምህርት ቤት ከመግለጽ ይቆጠቡ።
ሁሉንም አጠራጣሪ እና አናዳጅ/የጥቃት ባህሪ ሪፖርት ያድርጉ
ድንጋጌዎቻችንን የሚጥስ ማንኛውንም ሰው ብሎክ በማድረግ ሪፖርት ያድርጉ። ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ጥቂት የጥሰት ምሳሌዎች ናቸው:
  • የገንዘብ ጥያቄዎች
  • ትንኮሳ ወይም ማስፈራሪያዎች
  • መሳሳት ወይም ማውጣጣት
  • ማንኛውንም የግል መረጃ ስለ ያልተገባ ባህሪው በተፈጠሩብዎ ስጋቶች ላይ ተመስርተው ሪፖርት ማድረግ ይችላሉ
  • ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የማህበረሰብ መመሪያዎቻችንን ይመልከቱ።

የገጽ ለገጽ ደህንነት

እነ ማን ያውቃሉ?
ለጓደኛዎ ወይም ለቤተሰብዎ አባል ስለ እቅዶችዎ መቼና ወዴት እንደሚሄዱ ጨምሮ ይንገሯቸው። ሁልጊዜ ድንገተኛ ነገር ቢገጥምዎ እንኳ እንዲያገለግልዎ ስልክዎን መያዝዎን አይርሱ።
ህዝብ በሚገኝበት ቦታ ይገናኙ
ለመጀመሪያዎቹ ጥቂት ጊዜያት ሲገናኙ በፍጹም በመኖሪያ ቤትዎ፣ የመቀጣጠሪያ ቤትዎ ወይም ማንኛውም ሌላ ቀጠሮ የሚይዙበት ቦታ ሳይሆን ህዝብ በሚበዛበት፣ የህዝብ መገኛ ቦታ ይገናኙ። ቀጣሪዎ በግላዊ የመገናኛ ቦታ እንድትገናኙ ጫና የሚያሳድርብዎ ከሆነ መቀጣጠርዎን ወዲያውኑ ያቁሙ።
ቅድሚያ ለደህንነትዎ ይስጡ እንዲሁም ግልጽ የአእምሮ ዝግጅት እንዳለዎት ያረጋግጡ
እጾች ወይም የአልኮል መጠጦች የሚፈጥሩብዎትን ተጽእኖዎች ለይተው ይወቁ — እነዚህ ግምትዎን እና ጥንቃቄዎን ሊያዛቡ ይችላሉ። ቀጣሪዎ እርስዎ ከሚፈልጉት በላይ እጾችን ወይም የአልኮል መጠጥ እንድትወስዱ ጫና የሚያደርግብዎ ከሆነ እራስዎን በመግዛት ከዚህ በኋላ መቀጣጠርዎን ያቁሙ።
የትራንስፖርት አጠቃቀምዎን ይቆጣጠሩ
አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ በየትኛውም ጊዜ ጥለው መሄድ እንዲችሉ ወደ ቀጠሮዎ እንዴት እንደሚሄዱና እንደሚመለሱ አስበው መቆጣጠርዎ አስፈላጊ እንደሆነ ይሰማናል። እራስዎ የሚያሽከረክሩ ከሆነ እንደ የራይድ ማጋሪያ መተግበሪያ መጠቀም ወይም ጓደኛዎ ወይም የቤተሰብዎ አባል መጥቶ እንዲወስድዎ ማድረግ የመሳሰሉ ተለዋጭ እቅዶችን መያዝ ተመራጭ ሀሳብ ነው።
ምቾት ካልተሰማዎ ጥለው ይሂዱ
ሁልጊዜም ደመነፍስዎን ማመን እንዳለብዎት እናምናለን፤ ከባድ ወይም ምቾት የማይሰጥ ስሜት ከተሰማዎ ስሜቶችዎ ትክክል ስለሆኑ ቀጣሪዎን በመጀመሪያ ካሰባችሁት ጊዜ ቀድመው መሰናበት ጥሩ ነው። ይህን ካደረጉ የአስተናጋጅ ወይም አገልጋይን እርዳታ ይጠይቁ።
የግል እቃዎችዎን ያለ ጠባቂ አይተዉ

ሁልጊዜም አይንዎን የሚጠጡት መጠጥ ላይ ማድረግ እና መጠጡ ከየት እንደሚመጣ ማወቅ አለብዎት - በቀጥታ በአስተናጋጅ ወይም አገልጋይ የሚቀዳልዎትን መጠጥ ብቻ ይጠጡ። በመጠጦች ውስጥ ለወሲባዊ ጥቃት ለማመቻቸት ብዙ ጠረን፣ ቀለምና ጣእም የሌላቸው ንጥረ ነገሮች ይጨመራሉ።

ከዚህ በተጨማሪም ስልክዎን፣ ቦርሳዎን፣ የኪስ ቦርሳዎን እና ማንኛውንም የግል መረጃዎን የያዘ ነገርን ሁልጊዜም እራስዎ ይያዙ። እነዚህን እቃዎች ያለጠባቂ አለመተውዎን ያረጋግጡ።

የዳታ ደህንነትና አጭበርባሪዎች

የኮምፒውተር፣ ኢሜይልና የይለፍ ቃል ደህንነት

በኦንላይን መቀጣጠር ከመጀመርዎ በፊት ኮምፒውተርዎ 100% ደህንነቱ የተጠበቀ መሆኑን እና እርስዎንም ሆነ መረጃዎን ለአደጋ የማያጋልጥ መሆኑን ያረጋግጡ።

ከሁሉም የግልና የሥራ ዝግጅቶች የተለየ አዲስ የኦንላይን መቀጣጠሪያ ኢሜይል ይክፈቱ። ይህን በማድረግ የኦንላይን መቀጣጠር ግንኙነትን መከታተልና የትኛውንም አላስፈላጊ ወይም ያልተገባ ይዘት በቀላሉ መነጠል ይችላሉ።

አብይ ሆሄያት፣ ንዑስ ሆሄያት፣ ቁጥሮችና ልዩ ባህሪያትን ቀላቅሎ የያዘ የይለፍ ቃል መምረጥ አስፈላጊ ነው። በቀላሉ ሊገመት የሚችል የይለፍ ቃል አካውንትዎን እንዲጠለፍ ሊያደርግና ሲከፋም ጠላፊው ለመታወቂያ ስርቆት የግል ዝርዝሮችዎን ሊጠቀምባቸው ይችላል።

የግብረ ስጋ ግንኙነት ጤናና ፍቃድ

እራስዎን ይጠብቁ
ኮንዶሞች በትክክልና ወጥነት ባለው መልኩ ጥቅም ላይ የሚውሉ ከሆነ እንደ ኤችአይቪ በመሳሰሉ የአባላዘር በሽታዎች የመያዝና የማስተላፍ ስጋትን በእጅጉ ይቀንሳሉ።
ደረጃዎን ይወቁ
ሁሉም የአባላዘር በሽታዎች ምልክቶች ላያሳዩ የሚችሉ በመሆኑ እራስዎን እና የግብረ ስጋ ግንኙነት ጓደኛዎን መከላከል አስፈላጊ ነው። ጤናዎን ጠብቀው ይቀጥሉ እንዲሁም በቋሚነት በመመርመር የአባላዘር በሽታዎች ስር4ጭትን ይከላከሉ።
ስምምነት/ፍቃድ

ስምምነት በግብረ ስጋ ግንኙነት አድራጊዎች መካከል የግብረ ስጋ ግንኙነት ለማድረግ የሚደረግ ስምምነት ሁለቱም ወገኖች ስምምነታቸውን በግልጽና በነጻነት መግለጽ አለባቸው። የቃልና ማረጋገጫ ሰጪ የስምምነት መግለጫ እርስዎንም ሆነ የግብረ ስጋ ግንኙነት ጓደኛዎን አንዳችሁ የሌላኛችሁን ገደቦች እንድታከብሩ ይረዳችኋል።

እርስዎ ወይም የግብረ ስጋ ግንኙነት ጓደኛዎ ስምምነታችሁን በማንኛውም ጊዜ ልትሽሩ ይችላላችሁ። የግብረ ስጋ ግንኙነት ጓደኛዎ ምቾት ካልተሰማው ወይም እርግጠኛ ካልሆነ ወይም በእጽ ወይም የአልኮል መጠጥ ተጽእኖ ስር በመሆኑ ምክንያት ስምምነት መስጠት ካልቻለ አይቀጥሉ።

ምንጮች

በዩኤስ ውስጥ የሚገኙ የእርዳታና ድጋፍ ምንጮች:

በፍጹም ብቻዎን አይደሉም። በየትኛውም ፕላትፎርሞቻችን ላይ የሆነ ነገር ካጋጠምዎ ድጋፍ እንደምናደርግልዎ ልናረጋግጥልዎ እንወዳለን።

ወሲባዊ ጥቃትና ብዝበዛ

www.rainn.org/ | 800 656 4673

ህገወጥ የሰዎች ዝውውር

ብሔራዊ የሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ሆትላይን: 1-888-373-7888

የኤፍቢአይይኢንተርኔት ወንጀል ቅሬታ ማቅረቢያ ማዕከል

www.ic3.gov

እራስን ማጥፋትን መከላከል

https://988lifeline.org/ | 988

የቤት ውስጥ ጥቃት

1-800-799-SAFE (7233) ወይም 1-800-787-3224 | www.thehotline.org

የወንጀል ተጎጂ የድጋፍ ምንጭ ማዕከል

1-855-4VICTIM (855-484-2846) | www.victimconnect.org

የቀውስ የጽሁፍ መስመር

ፍቃደኛ የቀውስ አማካሪ ለማግኘት 'HOME' ብለው በ741741 የጽሁፍ መልእክት ይላኩ።